Equipment and Accessories
ገነቴ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በወልዲያ ከተማ ኮሪደር ልማት አገልግሎት የሚውል ብላክ ስማርት ፖል አቅርቦትና ገጠማ ስራ ህጋዊና ብቃት ካላቸው ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የአቅርቦትና ገጠማ ሥራ ማሰራት ይፈልጋል
Equipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsInstallation, Maintenance and Other Engineering Services
Amhara
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በወልድያ ከተማ አስተዳደር የሚገኘው የመንግስት የልማት ድርጅት የሆነው ገነቴ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በወልዲያ ከተማ ኮሪደር ልማት አገልግሎት የሚውል ብላክ ስማርት ፖል አቅርቦትና ገጠማ ስራ ህጋዊና ብቃት ካላቸው ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የአቅርቦትና ገጠማ ሥራ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ተሳታፊዎች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በሥራ ዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርቲፊኬት ያላቸውና የዘመኑን የስራ ግብር የከፈሉ፡፡ ሁሉንም ሰነዶቻቸውን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በተረጋገጠ ሲፒኦ የባንክ ጋራንቲ ዋና (ኦርጅናል) ዶክመንት ሰነዶች ጋር አያይዘው አብረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ቼክና ኢንሹራንስ ማቅረብ የተከለከለ በመሆኑ ቢቀርብ ተቀባይነትም የለውም፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ የጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ወልዲያ ከተማ በሚገኘው ገነቴ ኮንስትራክሽን ግዥና ፋይ/ንብ/አስ/ር ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ላይ ታሽጎ በሚቀጥለው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ላይ በኢንተርፕራይዙ ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይታገድም፡፡
- ጨረታ የሚከፈትበት ቀን የህዝብ በዓል የሚውልበት ከሆነ በማግስቱ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በብላክ ስማርት ፖል የአቅርቦትና ገጠማ ስራ ከመንግስታዊ የልማት ድርጅቶችና ከመንግስት ተቋማት የመልካም ስራ አፈጻጸም ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በሎት ጠቅላላ ድምር ይሆናል፡፡ የጨረታ አሸናፊም ሳምፕል በማቅረብ የቀረበውም ሳምፕል በአማካሪ መጽደቁ ተረጋግጦ የአቅርቦትና የገጠማው ስራው በራስ ወጭ ሳይት ድረስ መስራት ይኖርበታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ቫትንና ሌሎች ታክሰን ጨምሮ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መሙላት የተከለከለ ነው፡፡
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 09 13 50 49 72 /09 12 91 82 14 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ገነቴ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
Tender details
- Deadline: 2026-10-01
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-01 10:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: የገነቴ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Be'kur (Sep 21, 2026)
- Posted at: 2026-09-22T13:46:22.000Z
- Source: 2merkato