Equipment and Accessories
የግምቢ ፖሊ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጣና ኮሌጅ የኤሌክትሪክ፣ የውሃ ቧንቧ እና የኮንስትራክሽን ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የግምቢ ፖሊ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጣና ኮሌጅ በ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለሚሰጠው ሥልጠና የሚውል የኤሌክትሪክ፣ የውሃ ቧንቧ እና የኮንስትራክሽን ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተለውን የጨረታ መሥፈርት የሚያሞሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
1. ዕቃዎቹን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
2. የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉበትን ማስረጃ የሚያቀርቡ።
3. የታክስ ከፋይነት /TIN/ የተመዘገቡ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይ መሆናቸውን ማስረጃ የሚያቀርቡ።
4. ለጨረታ ማስከበሪያ ጠቅላላ ካቀረቡት ዋጋ 1% በተረጋገጠ ባንክ (CPO) ከጨረታ ሠነድ ጋር ማቅረብ አለባቸዉ።
5. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 100.00 በመክፈል ከኮሌጁ ግዥ እና ፋይናንስ አስተዳደር ሥራ ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
6. ተጫራቾች ሠነዱን ቀኑ ሲደርስ በጊምቢ ፖሊቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ኮሌጅ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን በስድስት ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ በ9 ሰዓት ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል ። ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን ይሆናል።
8. ተጫራቾች በጨረታዉ አሸናፊ ሆነው ሲቀርቡ ዕቃዎቹን በራሣቸዉ ማጓጓዣ እስከ ኮሌጁ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
9. ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
10. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 057 771 1872፣ 057 771 0005 በተንቀሳቃሽ ስልክ 09 11 91 67 33 / 09 19 29 40 17 ደዉለው ሊረዱ ይችላሉ።
የጊምቢ ፖሊ-ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ኮሌጅ
Tender details
- Deadline: 2026-10-10
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ6 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-10 15:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከቀኑ በ9 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Gimbi TVET College
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Sep 23, 2026)
- Posted at: 2026-09-23T08:32:03.000Z
- Source: 2merkato