Fuel and Lubricants
የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና አገልግሎት የሚውል የተሽከርካሪና ማሽነሪ ናፍታ፣ ዘይትና ቅባት በጥቅል አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ቁጥር-01/2019 ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና አገልግሎት የሚውል የተሸከርካሪና ማሽነሪ ናፍታ፣ ዘይትና ቅባት በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ በሎት በጥቅል አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ለዉድድር ይጋብዛል።
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN ያላቸው፣
3. ተጫራቾች የሚጠበቅባቸውን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
4, የግዥው መጠን ከብር 500,000.00 አምስት መቶ ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣
6. የሚገዙ የናፍታ፣ የተሽከርካሪና ማሽነሪ ዘይትና ቅባት ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፤
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመ/ቤቱ አካውንት ቁጥር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000013197966 በመክፈል የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ በመያዝ ከገንዘብ ያዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 09 ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ከ 13/01/2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ቀን 23/01/2019 ዓ.ም ማግኘት ይቻላል፤
8. ማንኛውም ተጫራች የማጫረቻ ሰነዱን ማለትም ዋናና ኮፒ (Original and Copy) በማለት በአንድ ኢንቨሎፕ በጥንቃቄ በማሸግ በኤጀንሲው ግዥ ኢፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት /በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ከ13/01/2019 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ቀን 23/01/-2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
9. ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ቫትና ሌሎች ታክስ እንዲሁምየትራንስፖርት ዋጋን ጨምሮ መሆን አለበት ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የዘይትና ቅባቱን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው፣ሆኖም የጠቅላላ ዋጋው 1% ከብር 2,000,000.00 /ሁለት ሚሊዮን ብር/ የሚበልጥ ከሆነ 2,000,000.00 /ሁለት ሚሊዮን ብር ብቻ ማስያዝ ይችላሉ፤
10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኤጀንሲው ዋና መ/ቤት ግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ በቀን----/01/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን 8፡30 ግዥ ኢፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 ይከፈታል፤
11. የጨረታው መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
12. ተጫራቾች በእያንዳንዱ የዋጋ መሙያ ገፅ ላይ ፊርማና መህተም ማድረግ አለባቸው፡፡ በተጨማሪም በዋጋ መሙያው ላይ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የጠፋ ከውድድር ውጭ ይደረጋል።
13. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከኤጀንሲው ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058-222-1100 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058-322-5155 /058- 222-1107 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
14. ኤጀንሲዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ባህር ዳር ፖ.ሣ.ቁ.382
አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ
Tender details
- Deadline: 2026-10-03
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-10-03 14:30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Amhara Rural Roads Construction Agency
- Bid bond: 1%፣ ሆኖም የጠቅላላ ዋጋው 1% ከብር 2,000,000.00 /ሁለት ሚሊዮን ብር/ የሚበልጥ ከሆነ 2,000,000.00 /ሁለት ሚሊዮን ብር ብቻ ማስያዝ ይችላሉ
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Sep 23, 2026)
- Posted at: 2026-09-23T08:58:12.000Z
- Source: 2merkato