Fuel and Lubricants
በሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር የደባርቅ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ሥር ለሚገኙት ሴክተር መስሪያ ቤቶች በመደበኛ በጀት ለ2019 ዓ.ም በጀት አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Fuel and LubricantsCleaning and Janitorial Equipment and ServiceBuilding and Finishing Materials
Amhara
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር የደባርቅ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ሥር ለሚገኙት ሴክተር መስሪያ ቤቶች በመደበኛ በጀት ለ2019 ዓ.ም በጀት አገልግሎት የሚውሉ
- ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያዎችና ሌሎች አላቂ እቃዎች፣
- ሎት 2. የመኪና መለዋወጫ /ስፔርፓርት/ ዕቃዎች፣
- ሎት 3. የመኪና ዘይት /ቅባቶች/፣
- ሎት 4. የመኪና ጎማዎች እና
- ሎት 5. የግንባታ ማቴሪያሎች ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ተጫራቾች ሊያሟሉት የሚገባቸው፡-
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ከግብር አስገቢው መ/ቤት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ተመዝጋቢ ለመሆናቸዉ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱት የግዥ መጠን ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙት የዕቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መገለጫ በእያዳንዳቸዉ ሎት ዝርዝር (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300 (ሶሰት መቶ ብር) በመሂ1 በመክፈል ደባርቅ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ከፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም ሲፒኦ /በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ጨረታው እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ ለግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ውስጥ ወይም ከኦርጅናል ጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ በማሸግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይሁን እንጅ የጨረታ ማስከበሪያ ጥሬ ገንዘብ ፖስታ ውስጥ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አይፈቀድም፡፡
- ያስያዙት ሲፒኦ (ጥሬ ገንዘብ) ከ2 በመቶ ቢያንስ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተጫራቾች ከውድድሩ ውጭ ይሆናሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ሰነዱን ሲሞላ ስርዝ ድልዝ ማድረግ አይፈቀድም እንዲሁም በአንድ ዋጋ ይሁን ጠቅላላ ድምር ዋጋ መሞላት አለበት ካልተሞላ ከዉድድር ዉጭ ይሆናል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ 5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ውል ማስከበሪያ 10 በመቶ (በሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ በማስያዝ ውል መያዝ ይጠበቅበታል፡፡
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ በጋዜጣ እትም ከወጣበት ቀን ህዳር 07/2019 እስከ ህዳር 16/2019 ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ሲሆን የመክፈቻ የመጨረሻ ቀን ህዳር 16/2019 ተጫራቾች ወይም ወኪሎች በተገኙበት በግ/ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 በዚሁ ቀን በ4፡00 ታሽጎ በ4፡30 በግልጽ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው፡፡
- ውድድር የሚካሄደው በሎት /በድምር/ ዋጋ ይሆናል፡፡
- የጨረታ መዝጊያ ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- መስሪያ ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የርክክብ ቦታ ከሎት.2 ዉጭ ያሉት በደ/ወረዳ ሴ/መ/ቤቶች ንብረት ክፍሎች ሲሆን ሎት 2 ጎንደር ከተማ ከሚጠገኑበት ይሆናል፡፡
- መስሪያ ቤቱ ለአሸናፊ ድርጅት ውል በሚሰጥበት ጊዜ ከጠቅላላ ዋጋው 20 በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብት አለው፡፡
- ስለ ጨረታው ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልጋቸው በስራ ሂደቱ ቢሮ ቁጥር 3 ዘወትር በስራ ሰዓት በአካል ቀርበው ወይም በስልክ ቁጥር058 117 00 11 /09 18 43 91 36 /09 18 06 58 17 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የደባርቅ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-25
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-11-25 10:30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Debarek Surrounding Woreda Finance and Economy Cooperation Bureau
- Bid bond: 2%
- Bid document price: ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300 (ሶሰት መቶ ብር)
- Published on: Be'kur (Nov 16, 2026)
- Posted at: 2026-11-16T14:08:16.000Z
- Source: Qelal Tenders