Textile, Garments and Uniforms

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለተለያዩ የሥራ ሂደቶች አገልግሎት የሚሰጡ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለተለያዩ የሥራ ሂደቶች አገልግሎት የሚሰጡ እቃዎች

  • ሎት 1 የደንብ ልብስ ብትን ጨርቅ፣
  • ሎት 2. ሽሚዝና ጫማ፣
  • ሎት 3. የጽህፈት መሳሪያዎች፣
  • ሎት 4. የህትመት ዉጤቶች፣
  • ሎት 5 ነዳጅና ቅባት፣
  • ሎት 6. የጽዳት እቃዎች፣
  • ሎት 7. ሌሎች አላቂ እቃዎች፣
  • ሎት 8. የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣
  • ሎት 9. የመኪና ጎማ፣
  • ሎት 10. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
  • ሎት 11. የፈርኒቸር እቃዎች፣
  • ሎት 12. የህንፃ መሳሪያዎች፣
  • ሎት 13. የቢሮ መጋረጃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊዉ ድርጅት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ 

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ሰርተፊኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት የምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸዉ፡፡
  2.  ተወዳዳሪዎች ተገቢዉን የታክስና የግብር ግዴታ የተወጡ መሆኑን የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  3. ተጫራቾች ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሸህ ብር) እና ከዚያ በላይ ለሚፈፀሙ ግዥዎች እና ኤሌክትሮኒክስ ነክ እቃዎች የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸዉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1- 3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  5.  የእቃዎቹን ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ከህዳር 7/2019 ዓ.ም ጀምሮ ለሎት የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ጎንደር ቋሚ ምድብ ችሎት የነበረዉ ግቢ ዉስጥ ቢሮ ቁጥር 10 ሙሉ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሎት ድምር ከሞሉት ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ስለሆነም የሞሉትን ዋጋ ደምረዉ ማስቀመጥ የሚገባቸዉ ሲሆን በንባብ ያቀረቡት ድምር ከአርቲሜቲክ የሂሳብ ማስተካከያ ስሌት በኋላ ከሶስት በመቶ በላይ ወይም በታች ከሆነ ከጨረታ ዉድድር ዉጭ ይሆናሉ፡፡
  8. ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ከህዳር 7/2019 ዓ.ም ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ላይ የሚቆይ ሲሆን ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ወጥ በሆነ ኦርጅናል በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ጎንደር ቋሚ ምድብ ችሎት ከነበረዉ ቢሮ ቁጥር 10 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት እስከ ህዳር 17/2019 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደ ቢሮ ቁጥር 10 በ17/3/2019 ዓ.ም 4፡00 ታሽጎ 4፡15 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በጨረታዉ አከፋፈት ወቅት ባይገኙም ጨረታዉ በተቀመጠዉ ቀንና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  10. የመጨረሻዉ የጨረታ ማሸጊያና መክፈቻዉ ቀን የህዝብ በዓላት ቀን ከሆነ ሰዓቱ እንደተጠበቀ ሆኖ በቀጣይ የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
  11. መስሪያ ቤቱ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡ ዉድድሩን በሎት ድምር ወይም በነጠላ ዋጋ የማወዳደር መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  12.  አሸናፊዉ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀለት ከ5 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ የዉል ማስከበሪያ በማስያዝ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዉስጥ ቀርበዉ ዉል መዉሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
  13. ጥያቄ ወይም ማብራሪያ ካለዎት ግዥና ፋይና/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 111 44 40 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-26
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-11-26 10:15
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: የማእከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Be'kur (Nov 16, 2026)
  • Posted at: 2026-11-16T13:59:35.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders