Stationery
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን የግዥና ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት በ2019 በጀት ዓመት አላቂ ዕቃዎችን፣ ቋሚ ዕቃዎችን እና የአገልግሎት ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ /የጨረታ ቁጥር 02/2019
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን የግዥና ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት በ2019 በጀት ዓመት አላቂ ዕቃዎችን (ቋሚ ቃዎችን እና የአገልግሎት ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 አላቂ የጽህፈት መሣሪያዎች
- ሎት 2 የመኪኖች ማስዋቢያ እቃዎች
- ሎት 3 የህትመት አገልግሎት
- ሎት 4 ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
- ሎት 5 የጽዳት እቃ
- ሎት 6 የደንብ ልብስና ስፌት
- ሎት 7ሌሎች አላቂ እቃዎች
- ሎት 8 የኤሌክትሮኒክስ ጥገና
- ሎት 9 የመኪና ጎማ
- ሎት 10 የፈርኒቸር እቃዎች
መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፡-
- ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ
- የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማቅረብ የሚችሉ፣
- ከገቢዎች የተጻፈ የአቅራቢነነት ደብዳቤ ያላቸው፣
- የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር Tin No / ያላቸው፣
- በመንግስተ ግዥና የንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ድረ-ገጽ (WWW.PPA.gov.et)
- ተጫራቾች የሚያስይዙት የጨረታ ማስከበሪያ/CPO
- ሀ. ሎት 1 አላቂ የጽህፈት መሣሪያዎች 10,000 ብር
- ለ. ሎት 2 የመኪና ማስዋቢያ 5,000 ብር
- ሐ . ሎት 3 የህትመት አገልግሎት 5,000 ብር
- መ ሎት 4 የቋሚ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 10,000 ብር
- ሰ ሎት 5 የጽዳት እቃዎች 5000 ብር
- ረ ሎት 6 የደንብ ልብስ 5,000 ብር
- ሸ ሎት 7 ሌሎች አላቂ እቃዎች 5,000 ብር
- ቀ ሎት 8 የኤሌክትሮኒክስ ጥገና-5,000 ብር
- በ ሎት 9. የመኪና ጎማ ግዥ 10,000 ብር
- ተ ሎት 10. የፈርኒቸር እቃዎች - 10,000 ብር
- ተጫራቾች በባንክ የተረጋገጠ በመ/ቤታችን ስም CPO ማስያዝ አለባችሁ ነገር ግን CPO ያላስያዘ ቢኖር ከጨረታ ውጪ ይሆናል።
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ለመወዳደር / ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ዕቃ ናሙና መቅረብ አለበት፣ እስፔስፍኬሽን ለሚያስፈልጋቸው ደግሞ በተረጋጋ መንገድ ሞርተው ያዝ።
- ማንኛውም ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1 እስከ 10 የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ 15ኛ ፎቅ የፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመቅረብና የማይመለስ 200 ብር ሁለት መቶ ብር ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- አሸናፊው ድርጅት ጥራቱን ያልጠበቀ ዕቃ ወይም አገልግሎት ካቀረበ በራሱ ወጪ የመለወጥ ግዴታ አለበት።
- መ/ቤቱ ካቀረበው ሰነድ ውጪ በሌላ ሰነድ በአማራጭነት ማቅረብ አይቻልም።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይናንሻል ኦርጅናልና ፋይናንሻል ኮፒ እና ቴክኒካል ኦሪጅናልና ኮፒ ቴክኒካል ዋጋ ሞልታችሁ በተናጠል (ለየብቻ በፖስታ አድርጋችሁ የድርጅታችሁን ማህተምና ፊርማ የተወዳደራችሁበትን የሎት አይነት በፖስታው ላይ እየጻፋችሁ አስገቡ፤ ካልጻፋችሁበት ደግሞ ፖስታችሁ እንደማይከፈት እያወቃችሁ የተባሉትን በሙሉ በማድረግ በጠቅላላ አገልግሎት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ወደ ህንጻው ስትገቡ በቀኝ በኩል ባለው ሊፍት 15ኛ ፎቅ ፊት ለፊት ለጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባችሁ።
- ጥቃቅና አንስተኛ ተጫራቾች ለምትጫረቱባቸው ዕቃዎች የጨረታ ሰንዱን በነፃ ለመውሰድ
ሀ. ካደራጃችሁ መ/ቤት ደብዳቤ ማምጣት አለባችሁ፤
ለ. ሰነዱን በነፃ ለመውሰድ በመመሪያ መሰረት ለምታቀርቡት ዕቃ አምራች መሆን አለባችሁ
15. ተጫራቾች መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት በትክከል መሙላት አለባቸው፤
16. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ አሸናፊው ድርጅት ባሸነፈበት ዕቃ ወይም አገልግሎት ላይ ውል ሲገባ የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል፤ እንዲሁም አሸናፊ የሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት ጨረታ ተከፍቶ ውጤት ከተለጠፈ ከ8 የሥራ ቀናት በኋላ በመ/ቤታችን ቀርቦ ውል መግባት አለበት።
17. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ጋዜጣው ከወጣበት ከ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል። ነገር ግን ከ11ኛው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለው የሥራ ቀናት ውስጥ የሚከፈት ይሆናል።
ማሳሰቢያ፡-
- ተጫራቾች የቀረበው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆኑንና ያላካተተ መሆኑን መግለጽ አለባችሁ ይህ ካልሆነ ግን መ/ቤቱ የቀረበውን ዋጋ ቫትን እንዳካተተ አድርጎ ይወስደዋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ክፍለ ከተማ፣ አራዳ ወረዳ 1 ፒያሳ እስታቲክስ ጎን ዋስትና ንግድ ማእከል አናት ህንጻ ፊት ለፊት 15ኛ ፎቅ ላይ ይገኛል
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-127-6825 ይደውሉ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን
Tender details
- Deadline: 2026-10-06
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጋዜጣው ከወጣበት ከ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-06 10:30
- Bid opening (note): ጋዜጣው ከወጣበት ከ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለሥልጣን
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 24, 2026)
- Posted at: 2026-09-24T08:25:25.000Z
- Source: Qelal Tenders