Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በየካ ክ/ከተማ በወረዳ 04 የቀበና ቅድመ አንደኛ ደረጃ፣ የመ/ደረጃ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የሚውሉ አላቂ የፅህፈት መሳሪያ፣ የደንብ ልብስ፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ለህትመት አገልግሎት፣ ቋሚ ዕቃዎች እና ሌሎችም አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በየካ ክ/ከተማ በወረዳ 04 የቀበና ቅድመ አንደኛ ደረጃ፣ የመ/ደረጃ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የሚውሉ አላቂ የፅህፈት መሳሪያ፣ የደንብ ልብስ፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ለህትመት አገልግሎት፣ ቋሚ ዕቃዎች እና ሌሎችም በ1ኛ ዙር ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
1. ተጫራቾች የተሰማሩበት የስራ መስክ የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸውና የታደሰ የንግድ ምዝገባ እና ፍቃድ ማስረጃ TIN No የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማቅረብ የሚችሉ
2. ተጫራቾች ዋጋው ቫትን ጨምሮ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት የጨረታውን ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ ዋጋውን ሞልተው ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያገለግል የመጫረቻ ዋጋ በቀበና ት/ቤት ስም
1. ለደንብ ልብስ ተጫራች፡- ብር 7,000.00 (ሰባት ሺህ ብር ብቻ)
2. ለአላቂ የቢሮ እቃዎችና ለአላቂ የትምህርት እቃዎች ተጫራች፡-ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር ብቻ)
3. ለህትመት አገልግሎት ተጫራች፡-ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር ብቻ)
4. ለሌሎች አላቂ እቃዎች ተጫራች፡-ብር 7,000.00(ሰባት ሺህ ብር ብቻ)
5. ለፕላንት፣ለማሽነሪ እና ለመሳሪያ መግዢያ ተጫራች፡-ብር 7,000 (ስባት ሺህ ብር ብቻ)
6. ለህንፃ፣ለቁሳቁስና ለተገጣጣሚ መግዢያ ተጫራች፡-ብር 7,000 (ስባት ሺህ ብር ብቻ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ) ብር የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይታሸግና 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 6 ይከፈታል።
5. አሸናፊ ተጫራቾች ውል ሲዋዋሉ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
6. ናሙና ያልቀረበበት የዘገየ ጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ የጨረታ ሰነድ ከጨረታ ሰነድ ውጪ ተሞልቶ የመጣ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም። በጨረታ ሰነድ 4.6 እና 9 የተቀመጡት ግዴታዎች ከሰነዱ ጋር ተሟልቶ ያላቀረቡ ተጫራቾች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
7. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት እራሳቸው አምርተው ለገበያ በሚያቀርቡት ዕቃ ካልሆነ በስተቀር የተዘጋጀ ዕቃ ምርት ገዝተው ለሚወዳደሩበት እንደማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ እና የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
8. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት ግዢ ፈፃሚ መጋዘን ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
9. ስርዝ ድልዝ መረጃዎች ተቀባይነት የላቸውም።
10. ት/ቤቱ ሰነዱ ላይ ካሰፈራቸው ውጪ ምንም ዓይነት የዋጋ፣ የውድድር እና የቴክኖሎጂ አማራጮችን አይቀበልም።
11. መስሪያ ቤቱ ለግዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. ሰነዱ ላይ ዋጋ ሞልተው ሲያስገቡ የሚወዳደሩበት ሎት መጨረሻ ላይ የእቃዎቹ ጠቅላላ ድምር ዋጋ ይገለፅ።
አድራሻ፡- ከቀበና አደባባይ ወደ ጀርመን ኤምባሲ በሚወስደው መንገድ ቤላ ገስት ሀውስ ጀርባ ላይ።
ስልክ፡- 011 1 26 12 85
የቀበና ቅድመ አንደኛ ደረጃ፣ የመ/ደረጃ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-07
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-07 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Kebena Kindergarten & Elementary School
- Buyer address: ከቀበና አደባባይ ወደ ጀርመን ኤምባሲ በሚወሰደው መንገድ ላይ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 25, 2026)
- Posted at: 2026-09-25T07:38:12.000Z
- Source: Qelal Tenders