House and Building Sale

የኮንደሚንየም ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

 የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍ/ባለመብት እነ ዳናይ ሙሉጌታ እና በፍ/ባለዕዳ ፍሊንት ስቶን ኢንጂነሪንግ አ/ማ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ 325781 በጥር 18 ቀን 2018 ዓ/ም እና መ/ቁ 325781 በ11/09/2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት 1ኛ በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 09 የሚገኝ የቤ.ቁ G-15 የይዞታ መለያ ቁጥር AA000030900023 ካርታ ያለው የሠፈሩ ስም ልደታ ኮንደሚንየም የወለል ቁጥር ምድር የቤቱ ስፋት 22.33ካ/ሜ ጠቅላላ የቦታ ስፋት 1848.96ካ/ሜ የጋራ መገልገያ ስፋት በፕሮፖርሽን 23.21ካ/ሜ ጠቅላላ በህንጻው የሚደርሰው ስፋት በፕሮፖርሽን 45.4ካ/ሜ ከግቢው የሚደርሰው የቦታ በፕሮፖርሽን 17.42ካ/ሜ ጠቅላላ ከግቢው የሚደርሰው ስፋት በፕሮፖርሽን 4.58ካ/ሜ የተፈቀደው የቤቱ አገልግሎት ለንግድ ሆኖ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ 4,099,715.76 ( አራት ሚሊዮን ዘጠና ዘጠኝ ሺህ ሰባት መቶ አስራ አምስት ከ76/100) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

2ኛበልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 09 የሚገኝ የቤ.ቁ G-28 የይዞታ መለያ ቁጥር AA000030900023 ካርታ ያለው የሠፈሩ ስም ልደታ ኮንደሚንየም የወለል ቁጥር ምድር የቤቱ ስፋት 84.86ካ/ሜ ጠቅላላ የቦታ ስፋት 1848.96 ካ/ሜ የጋራ መገልገያ ስፋት በፕሮፖርሽን 88.21ካ/ሜ ጠቅላላ በህንጻው የሚደርሰው ስፋት በፕሮፖርሽን 173.07ካ/ሜ ከግቢው የሚደርሰው የቦታ በፕሮፖርሽን 17.42ካ/ሜ ጠቅላላ ከግቢው የሚደርሰው ስፋት በፕሮፖርሽን 190.49ካ/ሜ የተፈቀደው የቤቱ አገልግሎት ለንግድ ሆኖ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ 15,581,701.02 ( አስራ አምስት ሚሊዮን አምስት መቶ ሰማንያ አንድ ሺህ ሰባት መቶ አንድ ከ02/100) ሆኖ የትራክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-27
  • Bid closing time: 11:00
  • Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-10-27 11:00
  • Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Addis Zemen (Sep 25, 2026)
  • Posted at: 2026-09-25T07:47:05.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders