Stationery

የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የመንግስት ግዥ አስተዳደር በ2019 በጀት አመት የሚያስፈልገዉን ቋሚ እና አላቂ የትምህርት እቃዎች እና ልዩ ልዩ እቃዎችን የአንደኛ ዙር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም

የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የመንግስት ግዥ አስተዳደር በ2019 በጀት አመት የሚያስፈልገዉን ıኛ ዙር ቋሚ እና አላቂ የትምህርት እቃዎች እና ልዩ ልዩ እቃዎችን የአንደኛ ዙር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ምዝገባና የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ የዘመኑ ግብር ስለመክፈላቸው ከከፈሉበት አግባብነት ያለዉ የግብር ክሊራንስ፣የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት እና የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።

1. ከጠቅላላ የግዥ ዋጋው ከ100,000 ብር በላይ ከሆነ ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል

2. የጨረታ ሰነዱ ለሎት የማይመለስ ብር 200 (ብር ሁለት መቶ) ብር በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ፋይናንስ ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 206 ድረስ በመምጣት መግዛት ይቻላል።

3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናል እና ኮፒ (ቴክኒካል ለብቻ ፖስታ፣ ፋይናንሽል ኦርጅናል በየሎቱ ለብቻቸው ፖስታ እና ኮፒ ለብቻ ፖስታ ሁሉም በአንድ ፖስታ) ጨረታው ከወጣበት ቀን እስከ 10 የስራ ቀን ድረስ በሰሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 205 በመምጣት በቢሮ በተዘጋጀው ውሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

4. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ በኮሌጁ የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 205 ይከፈታል።

5. ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ ከ2 ቀን በፊት ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ናሙና ለማይቀርብባቸው የእቃ አይነት በሚቀርበው እስፔስፍኬሽን መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ናሙናዎቹ በጨረታው ለተሸነፈ ተጨራቾች የሚመለሱ መሆናቸውን እንገልጻለን።

6. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ሆኖው የሚገኙበት እቃዎችን በአጠቃላይ ዋጋ 10 ፐርሰንት የውል ማስከበሪያ በማስያዝ የግዥ ውል ስምምነት መፈራረም ይኖርባቸዋል።

7. አሸናፊ ድርጅት የሚቀርቡትን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት እስከ ኮሌጁ ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

8. መ/ቤቱ/ኮሌጁ በጨረታ ሰነዱ ከተገለፀው የአቅርቦት መጠን ላይ መጨመር ወይም መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ ሊያገኘው በአሸናፊው ተጫራች የቀረበው ውድድሩ የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር እስከ 20% (ሃያ በመቶ) መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል።

9. የጨረታ ሰነድ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከሚከፈትበት ዕለት ጀምሮ ለ60 ቀናት ይሆናል። ኮሌጁ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተ.ቁ

የሎት ዝርዝር

ሲ.ፒ.ኦ መጠን

ሎት 1

የሰራተኞች ደንብ ልብስ

15,000

ሎት 2

የፅዳት ዕቃዎች

10,000

ሎት 3

የስቴሽናሪ እና ፕንተር ቀለም

10,000

ሎት 4

የሰራተኞች ደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት

10,000

ሎት 5

የእንጨት ት/ት ክፍል ዕቃዎች

100,000

ሎት 6

የኮንስትራችን ት/ት ክፍል እቃዎች

80,000

ሎት 7

የምግብ ዝግጅት ትምህርት ክፍል ዕቃዎች/ሆቴል

50,000

ሎት 8

የጋርመንት ት/ት ክፍል ዕቃዎች

70,000

ሎት 9

ማኑፋክቸሪንግ ትምህርት ክፍል ዕቃዎች

70,000

ሎት 10

ቤተ መጸሃፍት

10,000

ሎት 11

የከተማ ግብርና ትምህርት ክፍል ዕቃዎች

50,000

ሎት 12

የህንፃ አስተዳደር ጽ/ቤት የሚሆን ኤሌክትሪክ ዕቃዎች፤ የቧንቧ ዕቃዎች ለህፃናት ማቆያ የሚሆን ዕቃዎች

80,000

ሎት 13

ቴክኖሎጂ

80,000

ሎት 14

ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች (ፈርኒቸር እቃዎች)

80,000

ሎት 15

የአውቶ ሜካኒክ ት/ት ክፍል ዕቃዎች

100,000

ሎት 16

ህትመት ስራ

10,000

ሎት 17

የመኪና ዕቃዎቸ

30,000

ሎት 18

የአይሲቲ ዕቃዎች

100,000

አድራሻ፡- ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ወረዳ 10 ጀርባ ወይም መሪ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት አለፍ ብሎ ወይም መሪ 40/60 ኮንደሚንየም ጀርባ

ስልክ ቁጥር 01-18-93-26-75

የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-07
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-07 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Lemi Kura Manufacturing College
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር ለሎት
  • Published on: Addis Zemen (Sep 25, 2026)
  • Posted at: 2026-09-25T08:10:07.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders