Textile, Garments and Uniforms
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየካ ክፍለ ከተማ የየካ መሳለሚያ ጤና ጣቢያ የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየካ ክፍለ ከተማ የየካ መሳለሚያ ጤና ጣቢያ በ2019 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ግልፅ ጨረታ የወጣ።
- 6211 ሎት አንድ የደንብ ልብስ የስራ ልብስ CPO 9000 (ዘጠኝ ሺህ ብር)
- 6211 ሎት ሁለት የደንብ ልብስ የስራ ልብስ ስፌት CPO 5000 (አምስት ሺህ ብር)
- 6212 ሎት ሶስት አላቂ የቢሮ ዕቃዎች 7500 (ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብር)
- 6213 ሎት አራት የተለያዩ ህትመቶች CPO 7500 (ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብር)
- 6214 ሎት አምስት አላቂ እና ቋሚ የህክምና ዕቃዎች CPO 80000 (ሰማንያ ሺህ ብር)
- 6218 ሎት አራት ሌሎች አላቂ የፅዳት ዕቃዎች CPO 8000 (ስምንት ሺህ ብር)
- 6219 ሎት አምስት ልዩ ልዩ መሳሪያዎች CPO 5000 (አምስት ሺህ ብር)
- 6241 ሎት ስምንት የመኪና እድሳት እና ጥገናዎች CPO 3000 (ሶስት ሺህ ብር)
- 6243 ሎት ስምንት የማሽነሪ እድሳትና ጥገናዎች CPO 4000 (አራት ሺህ ብር)
- 6313 ሎት አስራ አንድ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች CPO 20000 (ሀያ ሺህ ብር)
- 6314 መጋረጃ ምንጣፍ እና ባለ መስታዎት የመድሀኒት መደርደሪያ(APTS) CPO 20000 (ሀያ ሺህ ብር)
በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል። በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ግለሰቦች እና ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
1. ከላይ ከተራ ቁጥር 1-11 የተጠቀሱትንና በሎት የተከፈሉትን ዕቃዎች አግባብነት ያለው ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣ የንግድ የምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፣ በጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚችሉ እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ ቲን ነምበር ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የካ መሳለሚያ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401 በመምጣት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከላይ ከተ.ቁጥር 1-11 የተጠቀሰውን ለእያንዳንዱ ሎት በመ/ ቤቱ ስም የተሰራ በ(CPO) ወይም በደብዳቤ እና ቢድ ቦንድ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
4. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ዕቃ ዋጋ ቫትን ጨምሮ ፋይናንሻል ኦርጂናል እና ኮፒውን በተለያየ በ(ሁለት) ፖስታ በየሎቱ በማሸግ ሙሉ አድራሻውን በመግለጽ የካ መሳለሚያ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
6. የጨረታ ሰነዱ የሚዘጋው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት መሆኑን እያሳወቅን የሚከፈትበት 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
7. ናሙና እንዲቀርብ በተባሉ ዕቃዎች ላይ ተጫራቾች ዋጋ ለሞሉበት ዕቃ ሳምፕል ወይም ናሙና ማቅረብ አለባቸው ናሙና ያላቀረበ ተጫራች ለዋጋ ውድድር አይቀርብም።
8. ጤና ጣቢያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
9. የጨረታ ሰነዱ ከመመሪያው ውጭ ሁሉም ሳይገነጠል መመለስ አለበት ሁሉንም የጨረታ ሰነድ ያልመለሰ መወዳደር አይችልም።
10. ሎት 2(6211 የደንብ ልብስ ስፌት) መስፊያ ማሽን መስሪያ ቤቱ ግቢ ውስጥ አምጥቶ መስፋት የሚችል መሆን አለበት።
አድራሻችን፡-ኮተቤ መምህራን ኮሌጅ አንድ ፌርማታ 200 ሜትር ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ለተጨማሪ መረጃ ስ/ቁጥር 011 865 6665
በየካ ክፍለ ከተማ የየካ መሳለሚያ ጤና ጣቢያ
Tender details
- Deadline: 2026-10-07
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-07 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: የየካ መሳለሚያ ጤና ጣቢያ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Sep 25, 2026)
- Posted at: 2026-09-25T08:19:46.000Z
- Source: 2merkato