Stationery
የደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ እና ለደሴ ትም/መሣ/ክዘ/ስርጭት ማዕከል ለ2019 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
StationeryOffice Supplies and ServicesCleaning and Janitorial Equipment and Service
Amhara
More tags
Equipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesBuilding and Finishing MaterialsConstruction and Water WorksSport Materials and EquipmentMusical InstrumentsArtMusic and EntertainmentSpare Parts and Car Decoration MaterialsTextile, Garments and UniformsTextile, Garment and LeatherShoes and Other Leather ProductsAmharic2merkatoDessie Teachers Education College
Description
ሀገር አቀፍ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ፣
የደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ እና ለደሴ ትም/መሣ/ክዘ/ስርጭት ማዕከል ለ2019 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ
- ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያ ፣
- ሎት 2 የጽዳት ዕቃ ፣
- ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ፣
- ሎት 4 የህንፃ መሣሪያ ፣
- ሎት 5 የስፖርት ዕቃ :
- ሎት 6 የሙዚቃ መሣሪያ ፣
- ሎት 7 የመኪና እቃ ፣
- ሎት 8 ደንብ ልብስ እና
- ሎት 9 ደንብ ጫማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣
- የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸው።
- የግዥው መጠን ብር 500,000.00/አምስት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች ኦርጅናል እቃ መሙላትና ያሸነፉባቸው እቃወች በባለሙያ ማስፈተሽና ማረጋገጥ አለባቸው።
- የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች በሰነዱ ላይ ዋጋ ሲሞሉ የእያንዳንዱ የእቃ ዋጋ ላይ ቫትን ጨምረው መሙላት አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300.00 ሶስት መቶ ብር ብቻ በመክፈል ከኮሌጁ ግዥ፣ ፋይ/ ንብ/አስ/ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 007 ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር ለሚወዳደሩበት ብር የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ ለሎት 1 ብር 33,386 (ሰላሳ ሶስት ሺህ ሶስት መቶ ሰማንያ ስድስት ብር ብቻ) ለሎት 2 ብር 22,217 ሃያ ሁለት ሽህ ሁለት መቶ አስራ ሰባት ብር ብቻ)፣ ለሎት 3 ብር 61,625 (ስልሳ አንድ ሺህ ስድስት መቶ ሃያ አምስት ብር ብቻ ፣ ለሎት 2 ብር 21,609 (ሃያ አንድ ሺህ ስድስት መቶ ዘጠኝ ብር ብቻ) ፣ ለሎት 5 ብር 2403 (ሁለት ሺህ አራት መቶ ሶስት ብር ብቻ)፣ለሎት 6 ብር 20,095 (ሃያ ሺህ ዘጠና አምስት ብር ብቻ) ሎት 7 ብር 106,974 (አንድ መቶ ስድስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባ አራት ብር ብቻ)፣ ሎት 8 ብር 7480/ሰባት ሺህ አራት መቶ ሰማንያ ብር ብቻ/ እና ሎት 9 ብር 7290/ሰባት ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና ብር ብቻ/ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከ73 ቀን ያላነሰ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬድት ማስያዝ አለባቸው።
- ውድድሩ የሚካሄደው በእቃዎቹ አይነት በሎት በጥቅል/ ጠቅላላ ድምር ነው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደሴ መም/ትም/ ኮሌጅ በግዥ፣ፋይ/ንብ/አስ/ደጋፊ የሥራ ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 007 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማለትም ከ /02/2019 ዓ/ም እስከ /03/2019 ዓ.ም ለ10 ተከታታይ ቀናት ጨረታውን መግዛትና በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ደጋፊ የሥራ ሂደት በቢሮ ቁጥር 007 በ11ኛው ቀን ከጧቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ላይ ይከፈታል የመክፈቻው ቀን የስራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው ቀን ከጧቱ 4 00 ታሽጎ 4፡30 ላይ ይከፈታል።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 007 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033,312,4220 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ ላይ የአንድ ዋጋም ጠ/ዋጋም ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ እንዲሁም ክፍት ያልተሞላ ካለ ከውድድር ውጭ ያደርጋል።
- የጨረታ ሰነድ ሲገዙ የተቀመጡ ሳምፕሎች ስላለ ሳምፕሉን ይመልከቱ።
- ተጫራቾች የጨረታ መመሪያ የተጫራቾች ዝርዝር መረጃ ሰንጠረዥ እና የግምገማ ዘዴና መስፈርት በሶፍት ኮፒ መውሰድ ይችላሉ።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡-
የመኪና እቃን በተመለከተ ጨረታው አመታዊ ማለትም መኪኖቹ ብልሽት ሲገጥመን የምንገዛ መሆኑን ውድድሩም በነጠላ ዋጋ መሆኑን እናሳስባለን።
የደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ
Tender details
- Deadline: 2026-11-20
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጧቱ 4፡00
- Bid opening: 2026-11-20 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጧቱ 4፡30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Dessie Teachers Education College
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: ለእያንዳንዱ ሎት 300.00 (ሦስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Nov 10, 2026)
- Posted at: 2026-11-10T09:03:17.000Z
- Source: Qelal Tenders