Stationery

ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ/የተ/የግ/ ኩባንያ ለቢሮ አገልግሎት የሚሆኑ የተለያዩ የፅህፈት መሳሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ጨረታ ቁጥር EAC 003/2019

1. ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ/የተ/የግ/ ኩባንያ ለቢሮ አገልግሎት የሚሆኑ የተለያዩ የፅህፈት መሳሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ከግዥው ጋር አግባብነት ያለው የ2019 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚገልፅ ወቅታዊ ደብዳቤ (Tax Clearance) ፣የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚገልፅ ማስረጃ፣ ቲን ሰርተፍኬት እና ቫት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት።

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ህዳር 07 2019 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30-6፡30 እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡30-11፡00 ድረስ እንዲሁም ቅዳሜ እስከ 6፡30 ድረስ ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ.የተ.የግ.ማህበር ጉርድ ሾላ ሴንቸሪ ሞል ፊት ለፊት ወይም ላሜ ዴይሪ ጀርባ ከኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ አጠገብ በሚገኘው ኢትዮ አግሪ ሴፍት ህንፃ ላይ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የምትወዳደሩበትን ዋጋ በመሙላት በሰም በታሸገ ፖስታ/Envelop/ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ህዳር 07/2019 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 4፡30 ድረስ ማስገባት የሚቻል ሲሆን በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡45 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 106 ይከፈታል።

4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት፡-

  • አንድ ዋና /Original /የጨረታ ሰነድ ለብቻው በታሸገ ፖስታ
  • እንድ ቅጂ /Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻው በታሸገ ፖስታ
  • ሁሉንም በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ውስጥ ተካቶ የታሸገ መሆን አለበት።
  • በዋናውና በቅጂው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ዋናው ተቀባይነት ይኖረዋል።
  • ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፤ የተሰረዘ ሰነድ በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል።

5. ተጫራቾች ለሚገዛው የፅህፈት ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር የጠቅላላ ዋጋ 2% /ሁለት ከመቶ/ የባንክ ክፍያ ማዘዣ /CPO/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ ለኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ/የተ/ የግል/ማህበር በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6. ከላይ የተገለፀውን መመሪያ ባልተከተሉ ተጫራቾች ላይ ወዲያውኑ ከጨረታ የሚሰረዙ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

7. ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር፡- 011-6-676204 ፋክስ ቁጥር 011-6-732006 መጠቀም ይችላሉ።

8. ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ. የተ.የግል ማህበር ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ. የተ.የግል ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-11-16
  • Bid closing time: 10:30
  • Bid opening: 2026-11-16 10:45
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethio Agri-CEFT Pvt.Ltd.Co.
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Nov 10, 2026)
  • Posted at: 2026-11-10T09:13:08.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders