Equipment and Accessories

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ሥራና ክህሎት ቢሮ የአርባ ምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳታላይት ኢንስቲትዩት ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ የሥልጠና መሣሪያዎች፣ አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎችን እና የጽዳት ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ሥራና ክህሎት ቢሮ የአርባ ምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳታላይት ኢንስቲትዩት በ2019ዓ.ም የሥልጠና ዘመን በተመደበለት የመደበኛ እና የካፒታል በጀት ለተለያዩ ዲፓርትመንቶች ማለትም ለቴክስታይል እና ጋርመንት፣ ለአግሮ ፕሮሰሲንግ፣ ለእንጨት ሥራ፣ ለማሸን፣ ለሜካኒክስ፣ ለኤለክትሮ ቴክኖሎጅ (ለባዮ ሜዲካል) ዲፓርትመንቶች ለሥልጠና፣ አገልግሎት የሚውል

  • ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ የሥልጠና መሣሪያዎች፣
  • አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎችን እና
  • የጽዳት ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል፡፡

  1. በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው/ያላትና፣ የዘመኑን ግብር ስለመከፈሉ ማረጋገጫ የሚያቀርብ፣ እና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው/ያላት/፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ/የሆነች የቲን ቁጥር /tin Number/ ያለው /ያላት
  2. በመንግሥት ግዥ አቅርቦት የተመዘገቡበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው/ያላት
  3. የዕቃውን ዋጋ በኮሌጁ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ብቻ ገፁን ሳይገነጣጥል ሞልቶ የሚያቀርብ
  4. የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ የዕቃዎች መለያ /specification/ ኮሌጁ ባዘጋጀው መሠረት ብቻ የሚያቀርብ/ የምታቀርብ፣
  5. የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፣
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማከበሪያ ዋስትና ብር 5000.00 /አምስት ሺህ ብር/ ብቻ በባንክ የተረጋገጠ /ሲፒኦ/ /CPO/ ከእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ጋር በማሸግ ማቅረብና ማስያዝ ይገባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን / Bid Document/ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአ/ም/ጭ ፖ/ቴ/ሳ/ ኢንስቲትዩት ከ/ሂ/ደ/ሥ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 03 ዘወትር በሥራ ሰዓት በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 ( ሁለት መቶ ብር) በመግዛት መውሰድ ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ በእያንዳንዱ ገፅ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውን ፣ ማህተምና አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው፡፡
  9. አጠቃላይ የማስረጃቸውን ኮፒ ከዋናው ጋር ተገናዝቧል የሚል ማህተም አርፎበት እና ተፈርሞበት ተያይዞ መቅረብ አለበት፣
  10. የሚቀርበው የመወዳደሪያ ሰነድ በሁለት ኮፒ ተዘጋጅቶ የዕቃው ነጠላ ዋጋ በአንድ ላይ በታሸገ ፖስታ ኤንቨሎፕ/ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15/አሥራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰነዱን ከገዙበት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ ቀን የሚያበቃው የሥራ ቀን ከሆነ በ15ኛ ቀን ከቀኑ በ10፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በቀጣዩ ቀን ልክ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የታሸገው ሣጥን በአ/ምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳታላይት ኢንስቲትዩት በቢሮ ቁጥር 7 ይከፈታል ቀኑ በዓል (ዝግ) ከሆነ በሚቀጥለው የሥራቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል
  11. ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ የዋጋ ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፣ እንዲሁም ከስፔስፊኬሽን ውጭ ዕቃ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  12. አሸናፊዎች የዋጋውን 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝና ውል መፈራረም አለባቸው፣
  13. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች ማሸነፉ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ቀን ድረስ በራሱ ትራንስፖርት ተቋሙ ድረስ ማቅረብና ማስረከብ አለበት፡፡
  14. ተቋሙ የተሻለ አማራጭ መንገድ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. የተጭበረበረ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም በሕግም ያስቀጣል፡፡

ለተጨማሪመረጃ፡- 0468810960/0910744129/0912056962

ደቡብ/ኢ/ክ/መ/ሥ/ክ/ቢ/አ/ም/ፖ/ቴ/ሳ/ኢንስቲቲዩት ደውለው ይጠይቁ።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ሥራና ክህሎት ቢሮ

የአርባ ምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳታላይት ኢንስቲትዩት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-24
  • Bid closing time: 16:30
  • Bid closing (note): ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛ ቀን ከቀኑ በ10፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-25 09:00
  • Bid opening (note): ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛ ቀን ከቀኑ በ10፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በቀጣዩ ቀን ልክ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: Arba Minch Poly Technic & Satellite Institute
  • Bid bond: 5000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Nov 10, 2026)
  • Posted at: 2026-11-10T10:37:54.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders