Building and Finishing Materials

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የኤሌክትሮኒክ፣ የግንባታ ግብዓት ጥራት ፍተሻ ማሸን፣ የጽሕፈት መሣሪያ እና የፅዳት ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን በ2019ዓ.ም በጀት ዓመት የኤሌክትሮኒክ፣ የግንባታ ግብዓት ጥራት ፍተሻ ማሸን ፣ የጽሕፈት መሣሪያ እና የፅዳት ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን በማሟላት መሣተፍ ይችላሉ፡፡

  • ተጫራቾች በዚሁ የንግድ ሥራ ዘርፍ የተሰማሩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ እንዲሁም የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  • በገቢዎች ባለሥልጣን የምዝገባ ሠርተፍኬት የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥርና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  • ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስራ አምስት /15/ የሥራ ቀናት ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን በአካል በመቅረብ ለእያንዳንዱ ሰነድ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመግዛትና በመሙላት ለኤሌስክትሮኒክስ እና የግንባታ ግብዓት ጥራት ፍተሻ ማሽን ጨረታ ሰነድ ቴክኒካል ኦርጅናልና ኮፒ፣ ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ እንዲሁም የጽሕፈት መሣሪያና ጽዳት ዕቃዎችን ጨረታ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በአስራ አምስተኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡
  • ጨረታው በዚሁ ዕለት ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለኤሌክትሮኒክስ 50,000.00 (ሃምሣ ሺህ ብር) የግንባታ ግብዓት ጥራት ፍተሻ ማሽን 160,000.00 /አንድ መቶ ስልሳ ሺህ ብር/ ለጽሕፈት መሣሪያ 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) ለጽዳት ዕቃዎች 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ ወይም በካሽ ከጨረታ ኦርጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ መ/ቤቱ ባዘጋጀው የዋጋ መሙያ ሰነድ ላይ ብቻ መጠቀም አለባቸው፡፡
  • የጨረታው አሸናፊ ጨረታ ማሸነፉን በጽሑፍ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከመ/ቤቱ ጋር ውል መፈራረም አለበት፡፡
  • መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አርባ ምንጭ

የቢሮ ስልክ ቁጥር 04618107051

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን


Tender details

  • Deadline: 2026-11-26
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አምስተኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-26 14:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አምስተኛው የሥራ ቀን ከሰዓት 8፡00 ሰዓት
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: South Ethiopian Regional Government Construction Authority
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: ለእያንዳንዱ ሰነድ ብር 100 (አንድ መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Nov 10, 2026)
  • Posted at: 2026-11-10T09:01:08.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders