Stationery

የደሴ አካል ተሀድሶ ማእከል ለ2019 በጀት አመት ለማእከሉ አገልግሎት የሚውሉ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የህንጻ መሳሪያዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የደንብ ጫማ፣ የህክምና እቃዎች፣ የህትመት ስራዎች፣ የመኪና ዘይት እና ቅባት፣ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች እና የፎቶ ኮፒና የኮምፒውተር ጥገና አገልግሎት አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የደሴ አካል ተሀድሶ ማእከል ለ2019  በጀት አመት ለማእከሉ አገልግሎት የሚውሉ

  • የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የህንጻ መሳሪያዎች፣ የደንብ ልብስ ፣
  • የደንብ ጫማ፣ የህክምና እቃዎች፣ የህትመት ስራዎች የመኪና ዘይት እና ቅባት፣
  • የመኪና መለዋወጫ እቃዎች የፎቶ ኮፒና የኮምፒውተር ጥገና አገልግሎት አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል

ስለሆነም፡-

1. የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው : የግብር መክፈያ ቁጥር /TIN/ ያለው የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፤ ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል።

2. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን የሚያሟላ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች የጨረታ መመሪያውንና የእያንዳንዱን እቃዎች ዝርዝር መግለጫ | Specification | የያዘ የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00/ ሶስት መቶ ብር / በመክፈል ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 7 መግዛት ይቻላል።

3. የጨረታ ማስከበሪያ በሞሉት ጠቅላላ ዋጋ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ /1%/ አንድ ፐርሰንት /ማቅረብ አለባችሁ።

4. የጨረታ ውድድሩ የሚደረገው በሎት ሆኖ በጠቅላላ ዋጋው ነው።

5. ጨረታውን በሚወዳደሩበት ጊዜ የተጋነነ ዋጋዎችን በገበያ ጥናት መሰረት በማድረግ ከውድድር ውጭ የምናደርግ መሆኑን እንገልፃለን።

6. የጨረታ ሰነዱ በታሸገ ፖስታ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ከ10ኛው ቀን ቀጥሎ በዋለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ በመቅረብ ቢሮ ቁጥር 7 በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ሳጥን ማስገባት ይጠበቃል።

7. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ተከታታይ የስራ ቀን ቀጥሎ በሚውለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ በእለቱ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማእከሉ ቢሮ ቁጥር 7 ጨረታው ይከፈታል።

8. ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሁሉም ተጫራቾች በአካል ባይገኙም በእለቱ የጨረታ ሰነዱ ተከፍቶ ከታየ በኋላ ተገቢው የጨረታ ማስከበሪያ መኖሩ ከተረጋገጠ ተጫራቹ በአካል ባይገኝም ጨረታው ይከፈታል።

9. የጨረታ አሸናፊው በተሰጠው የጨረታ ሰነድ /Specification/መሰረት ለማቅረብ ውለታ በወሰደበት ቀናት ውስጥ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ በማቅረብ በሚመለከታቸው ቴክኒክ ባለሙያ እየተረጋገጠ ለማእከሉ ን/ክፍል በሞ/19 ገቢ ማድረግ ይጠበቅበታል።

10. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 7 በአካል በመገኘት ወይም በቢሮ ስልክ ቁጥር 033 311 6263 - 033 312 4956 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የደሴ አካል ተሀድሶ ማእከል


Tender details

  • Deadline: 2026-11-21
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ተከታታይ የስራ ቀን ቀጥሎ በሚውለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30
  • Bid opening: 2026-11-21 10:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ተከታታይ የስራ ቀን ቀጥሎ በሚውለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Dessie Body Rehabilitation Center
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: ለእያንዳንዱ ሰነድ 300.00 (ሦስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Nov 10, 2026)
  • Posted at: 2026-11-10T08:53:13.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders