Building and Finishing Materials
የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ያገለገሉ የአልሙኒየም ፓርቲሽን እና መስታወቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር: ኢም.ገ/ግልጽ ጨረታ ቁ001/2019
- ኢትዮጵያ ምርት ገበያ ያገለገሉ የአልሙኒየም ፓርቲሽን እና መስታወቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
- ያገለገሉ የአልሙኒየም ፓርቲሽን እና መስታወት እቃዎች ከጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ህዳር 16 ቀን 2019 ዓ.ም. ድረስ ሜክሲኮ አልሳም ጨለለቅ ህንፃ 1 6ኛ ፎቅ ዘወትር በስራ ስአት ከሰኞ እስከ አርብ 2፡30-6፡30 ከሰአት 7፡30-10፡00፤ እንዲሁም ህዳር 16 ቀን 2019 እስከ ጠዋቱ 5፡00 ድረስ ብቻ በአካል በመገኘት ማስገባት ይቻላል፡፡
- ስለ አሻሻጡ የተዘጋጀውን ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን ሠነድ ሜክሲኮ አልሳም ጨለለቅ ህንፃ1 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 514 የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር ብቻ/ በቴሌ ብር በመክፈል ከጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ እስከህዳር 16 2019 ከጠዋቱ 5፡00 ድረስ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት የእቃ ዓይነት በጥቅል የጨረታ የመነሻ ዋጋቸውን10% (አስር ፐርሰንት የጨረታ ማስከበሪያ Bid Bond) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ለኢትዮጵያ ምርት ገበያ (Ethiopia Commodity Exchange) በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ህዳር 16 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 5፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮጵያ ምርት ገበያ አልሳም ጨለለቅ ህንፃ1 6ኛ ፎቅ ላይ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾቹ በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ በመቅረታቸው የጨረታውን መክፈት አያስተጓጉለውም፣
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡ ሁሉም እቃዎች የሚገኙበት ቦታ በኢትዮጵያ ምርት ገበያ በዋና መስሪያ ቤት አልሳም ጨለለቅ ህንፃ ሜክሲኮ የሚገኙ ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ ምርት ገበያ
Tender details
- Deadline: 2026-11-25
- Bid closing time: 11:00
- Bid opening: 2026-11-25 11:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Commodity Exchange (ECX)
- Buyer's registered address: Al-Sam Tower 2, 3rd Floor, Lideta
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Nov 10, 2026)
- Posted at: 2026-11-10T10:46:44.000Z
- Buyer website: https://www.ecx.com.et/
- Source: Qelal Tenders