Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በደ/ኢ/ክ/መንግስት የጎፋ ዞን የላሃ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ እና ፕላን ዩኒት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በላሃ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ስር ለሚገኙ ክላስተሮችና ዩኒቶች አገልግሎት የሚሆን ጽ/መሣሪያ እና የጽዳት ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 001/2019
በደ/ኢ/ክ/መንግስት የጎፋ ዞን የላሃ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ እና ፕላን ዩኒት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በላሃ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ስር ለሚገኙ ክላስተሮችና ዩኒቶች አገልግሎት የሚሆን ጽ/መሣሪያ እና የጽዳት ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡-
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን።
በዚህም መሠረት በጨረታዉ ላይ ለመሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች
1. ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው/ ያላት፣
2. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው/ያላት፣
3. የዘመኑ ግብር የከፈለ/ የከፈለች፣
4. የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር /TIN/ ያለው/ያላት፣
5. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ/የሆነች
6. የጨረታ ማስከበሪያ CPO 10,000/አስር ሺህ ብር/ ማስያዝ የሚችል/የምትችል፣
7. የአቅራቢነት ተመዝጋቢ መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል/ የምትችል፣
8. ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-7 የተጠቀሱትን ማስረጃዎችን ፎቶ- ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዶቻቸው ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ዘወትር በመንግስት ሥራ ሠዓት በላሃ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ዩኒት ቢሮ ቁጥር-6 ላይ ማስገባት ይችላል።
9. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ ማስተካከያ ጥያቄ ካላቸው ከጨረታ መክፈቻ ጊዜ ከ5 ቀን በፊት ለፋይናንስ እና ፕላን ዩኒት ማሳወቅ አለባቸው።
10. የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (Specification) ከጨረታ ሰነድ ላይ ማግኘት ይቻላል።
11. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ላይ የማይነበብና ስርዝ ድልዝ ያለው መሆን የለበትም።
12. የጨረታ ማስከበሪያ አሸናፊ ተጫራች እንደታወቀና ውል ከተፈራረመ በኋላ ለተሸናፊ ተጫራች ተመላሽ ይደረጋል።
ማሳሰቢያ፡-
1. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ ብር በመክፈል ከላሃ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር-6 በመንግስት ሥራ ሰዓት በየዕለቱ 2፡30 እና 6፡30 እስከ 7፡30 እስከ 11፡30 ድረስ ላይ ማግኘት ወይም መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃልን።
2. ተጫራቾች በገዙት ሠነድ ላይና በፖስታዎች ላይ የድርጅቱን ማህተም ማስቀመጥ አለበት
3. የጨረታው ሳጥን የሚታሸገው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ16ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
4. 16ኛው ቀን ቅዳሜና ዕሁድ ወይም በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው በሥራ ቀን ይሆናል።
5. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፋቸውን ዕቃዎችን በራሱ ወጪ በማጓጓዝ እስከ ላሃ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ እና ፕላን ዩኒት ንብረት ክፍል ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለበት።
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-የስ.ቁ 0913 116 126፣ 0986 731 042፣ 0926 265 970፣ 0928 969 624 ይደውሉ
የጎፋ ዞን ላሃ ከተማ አስ/ር ፋይናንስና ፕላን ዩኒት
ላሃ
Tender details
- Deadline: 2026-10-13
- Bid closing time: 09:30
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-13 10:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት
- Region: South Ethiopia Regional State
- Publishing entity: Gofa Zone Laha City Administration Finance Office
- Bid bond: 10,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 25, 2026)
- Posted at: 2026-09-25T09:20:39.000Z
- Source: Qelal Tenders