Vehicle

የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለወረዳው ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት አጠቃላይ በወረዳችን ውስጥ ለሚሰራው አዲስ የመንገድ ከፈታ፤ ነባር መንገድ በክፍል እና ሙሉ ጥገና ለማድረግ በዘርፉ ለተሰማሩ ማሽነሪ አቅራቢዎች ለመከራየት ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለወረዳው ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት አጠቃላይ በወረዳችን ውስጥ ለሚሰራው አዲስ የመንገድ ከፈታ፤ ነባር መንገድ በክፍል እና ሙሉ ጥገና ለማድረግ በዘርፉ ለተሰማሩ ማሽነሪ አቅራቢዎች በተቀመጠው ሰንጠረዥ መሰረት በሎት አንድ እና በሎት ሁለት ከፋፍሎ ለመከራየት ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት በጨረታው ላይ ለመወዳደር በምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዝቅተኛ መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

1. በዘርፉ ህጋዊና የታደስ የንግድ ፍቃድ ያለው/ላት እና በጀት ዓመትን ግብር የከፈላለች፣

2.በዘርፉ የንግድ የምዝገባ የምስከር ወረቀት ያለው እና ኮፒውን አያይዞ ማቅረብ የሚችል

3 የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ እና ኮፒውን አያይዞ ማቅረብ የሚችል

4.የቲን ነምበር/ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው/ላት እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡-

5. ተጫራቾች በጨረታው ላይ ሲወዳደሩ የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ወይንም የአከራይ ተከራይ ህጋዊ ውል ኮፒውን አያይዞ ማቅረብ የሚችል፣

6. ተጫራቾች በጨረታ ላይ ሲወዳደሩ የጨረታ ማስከበሪያ በሎት አንድ ላይ ብር 400,000 (አራት መቶ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

7. ተጫራቾች በጨረታ ላይ ሲወዳደሩ የጨረታ ማስከበሪያ በሎት ሁለት ላይ ብር 400,000 (አራት መቶ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

8. ጨረታው ለ21 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ በ21ኛው ቀን ከሰዓት 9፡00 ላይ ታሽጎ በ21ኛው ቀን ከሰዓት 9:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል።

9. ተጫራቾች የጨረታውን ዶክመንት ከደ/ቤ/ወ/ፋ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ከግዥና ንብረት አስ/ር ቢሮ ቁጥር 2/ ሁለት በአካል በመቅረብ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ዶክመንት መግዛት ይኖርባቸዋል።

10. ተጫራቾች የጨረታውን ዶክመንት ቴክኒካሉን 1 ኦርጅናል እና 2 ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሻሉን 1 ኦርጅና እና 2 ኮፒ ለየብቻ በማሽግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

11. ተጫራቾች ያስገቡት የጨረታ ዶክመንት ሙሉ ከሆነ ተጫራቾቹ ቢገኙም ባይገኙም የጨረታ ፖስታው ይከፈታል። ነገር ግን ዕለቱ ዝግ ወይንም በዓል ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

12. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተና ያላካተተ መሆኑን በግልጽ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል ፤ያለበለዚያ ያስገቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ ተደርጎ ይወሰዳል።

13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ፡-

ተጫራቾች በጨረታው ላይ አሽናፊ ሆኖ ሲገኝ አጠቃላይ የማሽነሪ ነዳጅ እና ቅባት እንዲሁም የማሸነሪዎች ጥገና ሰርቪስ በማሽነሪ አቀራቢ ድርጅት የሚሸፈን ሲሆን ተጫራች ለሰርቪስ አገልግሎት የሚውል ፒክአፕ ወይም “መኪና ማቅረብ ይኖርበታል።

 አድራሻ፡- የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

ደ/ወርቅ ስልክ /0929241731/0910997747

የደቡብ ቤንች /ወ/ፋ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-15
  • Bid closing time: 15:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከሰዓት 9፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-15 15:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከሰዓት 9፡30 ሰዓት
  • Region: South West Ethiopia Region
  • Publishing entity: South Bench Woreda F/E/D/Bureau
  • Buyer address: ደ/ወርቅ
  • Bid bond: 400,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 25, 2026)
  • Posted at: 2026-09-25T09:27:38.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders