Construction Machinery
የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን በተለያዩ የመንገድ ጥገና ፕሮጀክቶች ላይ ጠጠር የሚያመላልሱ ገልባጭ መኪኖች እስከነ ሎደሩ አቅራቢዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል
Description
ለመጀመርያ ዙር የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዢ መለያ ቁጥር ፡- ሴ/መ/ባ/009/2019
የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን በተለያዩ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ ጠጠር የሚያመላልሱ ገልባጭ መኪኖች እስከነ ሎደሩ አቅራቢዎችን ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የፕሮጀክቱ ስም |
በክልሉ ውስጥ የሚገኝበት ወረዳ |
የመንገዱ ርዝመት በኪ/ሜ |
|
1 |
ዳዋሌ ባሎ |
ሻፋሞ |
2.6 |
በዚሁ መሠረት
1. የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች መገልገያዎች የማከራየት ፍቃድ ያላቸው
2. ተጫራቾች አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ፡ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፡የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፊኬት፤ የግብር ከፋይነት ሰርተፊኬት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችላ የዘመኑን ግብር ከፈሉበትን ታክስ ከሊራንስ እንዲሁም PPA List እና EGP portal ውስጥ መመዝገባቸውን የሚያሳይ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. ከሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን ጋር ውለታ ገብቶ በአፈጻጸም ችግር ምክንያት ማስጠንቅቂያ ተሰቶት ስራውን ያላጠናቀቀ ውሉ የተቋረጠበት የገልባጭ መኪና አከራይ ድርጅት የጨረታ ሰነዱን መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችልም።
4. አዲስ ፍቃድ ያላቸው አንድ ፕሮጀክት እና የሥራ ልምድ ያላቸው ሁለት ፕሮጀክት ብቻ መወዳደር ይችላሉ ።
5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 300.00 (ሦስት መቶ ብር ) ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (ለአስር ) ተከታታይ ቀናት ከባለሥልጣኑ መ/ቤት ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁ -5 ቀርበው መግዛት ይችላል።
6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ በሁነታ ላይ ያልተመረተ ዋስትና (unconditional Bid bond) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጫራቾች የሚቀረበው የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 0.5% ማስያዝ ያለባቸው ሲሆን ተጫራቾች የሚቀረቡት የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከላይ የተገለጸው መሰረት ይሆናል። ከባንክ የሚቀረበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid bond) ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።
7. ገልባጭ መኪና እስከነሎደር የስሪት አመን እ.አ.አ 2012 እና ከዚያ በላይ ሆኖ የተሽከርካሪ የመጫን አቅም 14 ሜ.ኩ የሆነ ማቅረብ የሚችሉ።
8. የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መመርያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ (Bid security)፤ ፋይናሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል )እና ሁለት ኮፒዎችን እንድሁም ቴክንካል አንድ ዋና (ኦርጅናል ) እና ሁለት ኮፒ ሰነዶች በተለያየ ፖስታ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ ተካተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሠነድ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሠነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት። ሆኖም የተጠቀሰው ቀን የእረፍት ወይም የህዝብ በዓል ቀን ሆኖ ከዋለ በቀጣይ በስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል።
9. ጨረታ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወከሎቻቸው በተገኙበት ከላይ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ በባለስልጣኑ መ/ቤት አደራሽ ይከፈታል።
10. ባለስልጣኑ መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር፡- 046 212-446
የሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን
Tender details
- Deadline: 2026-11-30
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-30 14:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
- Region: Sidama
- Publishing entity: Sidama Roads Authority
- Bid bond: ከጠቅላላ ዋጋ 0.5%
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Nov 20, 2026)
- Posted at: 2026-11-20T07:57:59.000Z
- Source: Qelal Tenders