Construction Machinery and Equipment
የመቻራ ሚጨታ ከተማ መስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የውስጥ ለውስጥ መንገድ ለማሰራት የGRADER እና Dozer ማሽነሪዎች ክራይ አገልግሎት ግዥ ጨረታ አውጥቷል
Description
ለመንገድ ስራ የሚሆኑ ማሽነሪ ክራይ (Machinery Lease) ዓቅርቦት ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምስራቅ ኦሮሚያ ዞን የመቻራ ሚጨታ ከተማ መስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በመቻራ ሚጨታ ከተማ ማስተዳደር የከንቲባ ጽ/ቤት ባጀት በመቻራ ሚጨታ ከተማ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ለማሰራት ማሸነሪ ክራይ ስለሚፈልግ ለዚህም ስራ የሚውሉ ማሽነሪዎችን፡-
- GRADER A250 ሰዓት ነዳጅን ችለው ጨምሮ)
- Dozer D7R ለ400 ሰዓት ነዳጅን ችለው (ጨምሮ) ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን ማህበራት/ በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ የማሽነሪ አቅርቦት ፍቃድ ያላችሁ ድርጅቶች ማህበራት እንድትወዳደሩ ተጋብዛችኋል።
1. ተወዳዳሪዎች የታደሰ ንግድ ፍቃድና የዚህን ዓመት /የ2019 ግብር የተከፈለበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
2. ተወዳዳሪዎች በማሽነሪ ዓቅርቦት ፍቃድ የምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
3. ተወዳዳሪዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ NAT) ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
4. ተወዳዳሪዎች የ50,000 /የሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ህጋዊ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣
5. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መረጃ የያዘ ሠነድ የማይመለስ 1500 /አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከመቻራ ሚጨታ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ፣
6. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት /15/ የስራ ቀናት ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ ይቆያል፣
7. ተወዳዳሪዎች የገዙትን የጨረታ ሰነድ ሞልተው ኦሪጂናሉንና አንዱን ኮፒ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ አስራ አምስት /15/ ቀናት ውስጥ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፣
8. ተወዳዳሪዎች የመወዳደሪያ ሠነዱን በጥንቃቄ እንዲሞሉ እያሳሰብን በየትኛውም መልኩ ስርዝና ድልዝ ተቀባይነት የለውም፣ ወይም ከፊትለፊት የተፈረመ መሆን ይኖርበታል፣
9. ጨረታው በ16ኛው በአስራ ስድስተኛው/ቀን ከቀኑ 4:00 ሰዓት ላይ ታሽጎ ከቀኑ 8:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፣
1ዐ. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው በተባለው ሰዓት ይከፈታል፣
11. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በአጋጣሚ ከስራ ቀን ውጪ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፣
12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
13. ተወዳዳሪዎች ጨረታውን ካሻነፉበት ዋጋ ላይ 10% የሚሆን ብር (performance bond) ለማስያዝ ፍላጎት ያለው መሆን አለበት።
አድራሻ፡- በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምስራቅ ኦሮሚያ ዞን የመቻራ ሚጨታ ከተማ መስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-12-05
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው /በአስራ ስድስተኛው/ቀን ከቀኑ 4:00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-12-05 14:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው /በአስራ ስድስተኛው/ቀን ከቀኑ 8:30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Mechara Micheta City Administration Finance Office
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 1500.00 /አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር/
- Published on: Addis Zemen (Nov 20, 2026)
- Posted at: 2026-11-20T07:16:37.000Z
- Source: Qelal Tenders