Construction Machinery and Equipment

የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን በተለያዩ የመንገድ ጥገና ፕሮጀክቶች ላይ ጠጠር የሚያመላልሱ ገልባጭ መኪኖች እስከነ ሎደሩ አቅራቢዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል

Description

ለመጀመርያ ዙር የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የግዢ መለያ ቁጥር ፡- ሲ/መ/ባ/008/2019

የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን በተለያዩ የመንገድ ጥገና ፕሮጀክቶች ላይ ጠጠር የሚያመላልሱ ገልባጭ መኪኖች እስከነ ሎደሩ አቅራቢዎችን ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የፕሮጀክቱ ስም

በክልሉ ውስጥ የሚገኝበት ወረዳ

የመንገዱ ርዝመት በኪ/ሜ

1

ዝግባ መገንጠያ ሎካ አባያ ሎት 1

ዳሌ-ሎካ አባያ

10

2

ዝግባ መገንጠያ ሎካ አባያ ሎት 1

ሎካ አባያ

10

3

ጭሬ ላሌሳ ጉቦ ሄማ

ጭሬ

15

4

ጎርቼ ሀሮሽፋ ቱትቻ ጠጥቻ

ቡርሳ ጠጥቻ

18

5

ይርጋለም ቦካሶ

ወንሾ

7.5

6

አለታ ወንዶ አለታ ጩኮ

አለታ ጩኮ

6.6

7

ቦካሶ ኦሮዎ

ወንሾ

16

8

ጃራ ዳዶ ባሌላ መገንጠያ

ዶሬ

10.5

9

ዳምለ ጭራቻ ባዳሎ

ቦና

15

10

ባሌላ መገንጠያ ዳራራ ጩኮ

ቦርቻ -ዳራራ- ሎካ አባያ

37.3

11

ቃባዶ አበራ ሁላ

ዳራ

20

12

ታንካሮ ዳማካላ አሳራዶ ዎዮ

ሻፋሞ- ቦና

11

13

ባርቱ ቡክቶ

ሎካ አባያ

15

በዚሁ መሠረት

1. የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች መገልገያዎች የማከራየት ፍቃድ ያላቸው

2. ተጫራቾች አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ፡ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፡ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፊኬት፤ የግብር ከፋይነት ሰርተፊኬት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር ከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም PPA List እና EGP portal ውስጥ መመዝገባቸውን የሚያሳይ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ከሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን ጋር ውለታ ገብቶ በአፈጻጸም ችግር ምክንያት ማስጠንቅቂያ ተሰቶት ስራውን ያላጠናቀቀ ውሉ የተቋረጠበት የገልባጭ መኪና አከራይ ድርጅት የጨረታ ሰነዱን መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችልም።

4. አድስ ፍቃድ ያለቸው አንድ ፕሮጀክት እና የሥራ ልምድ ያላቸው ሁለት ፕሮጀክት ብቻ መወዳደር ይችላሉ ።

5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 300.00 (ሦስት መቶ ብር ) ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዘጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (ለአስር ) ተከታታይ ቀናት ከባለሥልጣኑ መ/ቤት ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁ -5 ቀርበው መግዛት ይችላል።

6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመረተ ዋስትና (unconditional Bid bond) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጫራቾች የሚቀረበው የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 0.5% ማስያዝ የለባቸው ሲሆን ተጫራቾች የሚቀረቡት የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከላይ የተገለጸው መሰረት ይሆናል። ከባንክ የሚቀረበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid bond) ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።

7. ገልባጭ መኪና እስከነሎደር የስሪት አመን እ.አ.አ 2012 እና ከዚያ በላይ ሆኖ የተሽከርካሪ የመጫን አቅም 14 ሜ.ኩ የሆነ ማቅረብ የሚችሉ።

8. የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መመርያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ (Bid security)፤ ፋይናሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል )እና ሁለት ኮፒዎችን እንድሁም ቴክንካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒ ሰነዶች በተለያየ ፖስታ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ ተካተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ህጋዊ የሆነ ማዕተም በመምታት ይህ ማስታዎቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ከፍል ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሠነድ ማስከበሪያው ከተክኒካል ሠነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት። ሆኖም የተጠቀሰው ቀን የእረፍት ወይም የህዝብ በዓል ቀን ሆኖ ከዋለ በቀጣይ በስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል።

9. ጨረታ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት ከላይ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ በባለስልጣኑ መ/ቤት አደራሽ ይከፈታል።

10. ባለስልጣኑ መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር፡- 046 212-446

የሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን


Tender details

  • Deadline: 2026-11-30
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-30 14:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
  • Region: Sidama
  • Publishing entity: Sidama Roads Authority
  • Bid bond: ከጠቅላላ ዋጋ 0.5%
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Nov 20, 2026)
  • Posted at: 2026-11-20T07:55:07.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders