Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በየካ ክ/ከተማ ጤ/ጽ/ቤት ጉራራ ጤና ጣቢያ የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

1ኛ ዙር አጠቃላይ ግዥ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በየካ ክ/ከተማ ጤ/ጽ/ቤት ጉራራ ጤና ጣቢያ

  • ሎት 1፡- የደንብ ልብስ
  • ሎት 2፡- የደንብ ልብስ ስፌት
  • ሎት 3፡- የጽዳት እቃዎች
  • ሎት 4፡- ጽህፈት መሳሪያ
  • ሎት 5፡- ፕላንትና ማሽነሪ (ቋሚ እቃ)
  • ሎት 6፡- አላቂ የህክምና መሳሪያዎች
  • ሎት 7፡- ህትመት
  • ሎት 8፡- የብረታብረት ስራዎችና የቢሮ እቃዎች ጥገና
  • ሎት 9፡- የሮቶ እጥበት አገልግሎት
  • ሎት 10፡- የጭነት እና ትራንስፖርት አገልግሎት
  • ሎት 11፡- ኤሌክትሮኒክስ (ኮምፒውተር፣ ፎቶኮፒና ፕሪንተር) ጥገና
  • ሎት 12፡- ባዮሜዲካል ጥገና አገልግሎት
  • ሎት 13፡- ባዮሜዲካል ሰርቪስ
  • ሎት 14፡- የቧንቧ መስመር ስራዎች
  • ሎት 15፡- የታፒሴሪ ስራ
  • ሎት 16፡- የኤሌክትሪክ ጥገና ስራዎች

ስለሆነም በጨረታ ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

1. ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የእቃና የአገልግሎት አቅራቢዎችዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ ፤ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ።

3. ተጫራቾች ናሙና ማቅረብ ግዴታ ይኖርባቸዋል (ለሎት 1፣3፤4፣5)

4. ግብር የመክፈል ግዴታ የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው

5. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 ብር (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በጉራራ ጤ/ጣቢያ ግዥ ክፍል ጨረታው ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ከ18/01/2019 ዓ/ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ሐሙስ ጠዋት ከ2፡30-6፡00 እና ዓርብ ከ2፡30-5፡00 እና ከሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ከ7፡30-11፡00 ድረስ መግዛት ይችላሉ።

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት 10,000.00 ብር (አስር ሺህ ብር) ሲፒኦ በማሰራት ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ወይም ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ አንድ ተጫራች አንድ ሎትና ከዚያ በላይ የሚገዛ ከሆነ ለእያንዳንዱ ሎት ሲፒኦ ማሰራት ይጠበቅበታል (ከሲፒኦ ውጭ የሆኑ ዋስትናዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም።

7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ፖስታ ለይቶ በማሸግ የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለጽ በታሸገ ኢንቬሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከ18/01/2019 ዓ/ም ጀምሮ በአስራ አንደኛው የስራ ቀን 4፡00 ድረስ ፈረንሳይ ለጋሲዮን ብረት ድልድይ የሃ ት/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው ጉራራ ጤ ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ግዥ ቢሮ በመቅረብ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

8. ተጫራቾች በሙሉ ወይም በከፊል መወዳደር ይችላሉ።

9. ተጫራቾች ከውድድር በኋላ አሸናፊ ከሆኑ ላሸነፉት እቃ የጠቅላላ ዋጋውን 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

10. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት በ11ኛው የስራ ቀን በ02/02/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ በዚያኑ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በጽ/ቤቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

11. መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይምበከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0910275044 መደወል ይቻላል

አድራሻ፦ ፈረንሳይ ለጋሲዮን ብረት ድልድይ የሃ ት/ቤት ፊት ለፊት

በየካ ክ/ከተማ ጤ/ጽ/ቤት ጉራራ ጤና ጣቢያ 


Tender details

  • Deadline: 2026-10-12
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-10-12 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Gurara Health Post
  • Bid bond: 10,000.00 (አስር ሺ ብር) ለእያንዳንዱ
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 26, 2026)
  • Posted at: 2026-09-28T07:54:45.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders