Cleaning and Janitorial Equipment and Service

የአማራ ብሔ/ክ/መ/የሰ/ሸዋ/ዞን የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ግ/ን/አሰ/ቡድን ለተለያዩ ሴ/መስሪያ ቤቶች የተለያዩ ቋሚ እና አላቂ ማቴሪያሎች ለ2019 ዓ.ም አገልግሎት የሚውሉ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2019

የአማራ ብሔ/ክ/መ/የሰ/ሸዋ/ዞን የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ግ/ን/አሰ/ቡድን ለተለያዩ ሴ/መስሪያ ቤቶች የተለያዩ ቋሚ እና አላቂ ማቴሪያሎች ለ2019 ዓ.ም አገልግሎት የሚውሉ ለመግዛት ይፈልጋል።

  1. የጽህፈት መሣሪያ ሎት 1 የጨረታ ማስከበሪያ 80000
  2. የጽዳት እቃዎች ሎት 2 የጨረታ ማስከበሪያ 15000
  3. ኮምፒውተርና ተዛማጅ ሎት 3 የጨረታ ማስከበሪያ 80000
  4. ኤሌክትሮኒክስ ሎት 4 የጨረታ ማስከበሪያ 10000
  5. የተለያዩ መጋረጃ እና ምንጣፍ ሎት 5 የጨረታ ማስከበሪያ 10000
  6. የመኪና ጥገና ሎት 6 ለ2ኛ ጊዜ የሠጣ የጨረታ ማስከበሪያ 10000 ብር
  7. የመኪና መለዋወጫ ሎት 7 ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስከበሪያ 20000

ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ከ16/1/2019 ዓ.ም እሰከ 25/1/2019 ዓ.ም ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ወዲያውኑ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

1. በጨረታ የሚሣተፍ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ የግብር ከፉይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር የቫት ተመዝጋቢ የተጨማሪ እሴት ታክስ መረጃውን አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤

2. በሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ላይ የጨረታ መዝጊያ ሰዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ማሻሻያ ማድረግና ራሳቸውን ከጨረታው ማግለል አይችለም።

3. ተጫራቾች የሞሉበትን የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ቢድ ቦንድ ወይም የባንክ ዋስትና እንዲሁም ከባንክ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ አለባቸው።

4. የንግድ ፍቃድና የመሣሠሉት መረጃዎች ከኦርጅናል ዶክመንት ጋር ተያይዘው መቅረብ አለባቸው።

5. በፖስታው ላይና እንዲሁም የጨረታ ዋጋ መሙያ የጨረታ ሠነድ ላይ የተጫራቾች ስምና ፊርማና ማህተም ሊኖረው ይገባል።

6. በሌላ ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።

7. በአንዱ ዋጋ ላይ ሆነ በጠቅላላ ድምር ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ስርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታ ውጪ ይሆናል።

8. ተጫራቹ ጠቅላላ ድምር አጠቃሎ ያልደመረ ከጨረታ ውጪ ይሆናል።

9. ተጫራቹ ጠቅላላ የደመረው እና ትክክለኛ አርቲሜቲክ ቼክ ተሰርቶ ልዩነቱ ከ3% በላይ ወይም በታች ከሆነ ከጨረታ ውድድር ውጪ ይሆናል።

10, ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ 5 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባሉት ተከታታይ ቀናት ውስጥ በጽ/ቤታችን በመገኘት የውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ ውል መፈፀም አለባቸው በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርበው ውል ካልፈፀሙ በግዥ መመሪያው መሠረት የጨረታ ማስከበሪያውን ውርስ በማድረግ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።

11. ተጫራቾች በጨረታ አፈፃፀም ሂደት ላይ ቅሬታ ካላቸው በግዥ አዋጅ መሠረት አሸናፊነቱ በተገለፀ በተከታታይ በ5 የስራ ቀን ውስጥ ቅሬታውን ማቅረብ ይችላሉ፤

12. ለአሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያሲያዙትን ብር ከአሸናፊ ተጫራች ጋር ውል እንደተፈፀመ ተመላሽ ይደረጋል።

13. በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን ሁሉንም ተጫራቹ መሙላት አለበት ሁሉንም ካልሞሉ ከውድድር ውጪ ይደረጋል።

14. ጨረታው በሚከፈትበት ወቅት የህዝብ በዓላት፣ ቅዳሜና እሁድ ከዋለ በቀጣዩ የስራ ቀናት በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

15. የጨረታ ሰነዱን በመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በመምጣት ብር 200 /ሁለት መቶ ብር በማይመለስ መግዛት የሚቻል ሲሆን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛትና መውሰድ ይችላሉ።

16. ሂሳብ የሚከፈለው አሸናፊው ተጫራች በውሉ መሰረት እቃዎቹን ሲያጠናቅቅ ክፍያን ይወስዳል።

17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

18. አሸናፊ የሚለየው በጥቅል ወይም በተናጠል መብቱ የሚያዋጣ ነው።

19. የተለያዩ ሌሎች ሳምፕል ለሚያስፈልጋቸው ሣምፕሉን በማየት ዋጋ በመሙላት ማቅረብ አለባቸው።

20. ከ500 ሺህ ብር በላይ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለበት።

21. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ሲፈልጉ በስልክ ቁጥር 0116851461/0106 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።

22. ለጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ ለተደራጁ ተጫራቾች በመመሪያ ቁጥር 144/2018 ልዩ አስተያየት ይደረግላቸዋል።

የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-06
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-10-06 10:30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: North Shewa Zone Menze Gera Medere Woreda F/E/D/B
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 26, 2026)
  • Posted at: 2026-09-28T08:58:54.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders