Printing and Publishing

የጋምቤላ ሕ/ብ/ክ/መንግስት ፋይናንስ ቢሮ ለፋይናንስ ግልጽነትና ተጠያቂነት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የህትመት አይነቶችን የማሳተም አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 0001/2019

የጋምቤላ ሕ/ብ/ክ/መንግስት ፋይናንስ ቢሮ ለፋይናንስ ግልጽነትና ተጠያቂነት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የህትመት አይነቶችን የማሳተም አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት ተጫራቾች:-

1. ተጫራቾች በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

2. ተጫራቾች በመ/ቤቱ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የሥራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከቢሮ ቁጥር 30 መግዛት ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸውና የዘመኑን እንቅስቃሴ የሚያመለክት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

4. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በቅድሚያ የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ወይምበባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ለሚጫረቱበት ዋጋ ብር 30000 (ሰላሳ ሺህ ብር) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤

5. ተጫራቾች የአቅራቢነት የምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6. የዋጋ ማቅረቢያና ሌሎች መረጃዎች የያዘው የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናልና ኮፒ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።

7. ጨረታው የሚከፈተው የጨረታ ማስታወቂያ በወጣበት ቀን መስከረም 16/1/2019 በ16ኛው ቀን እስከ 3፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው። ጨረታው በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ታሽጎ በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል።

8. የጨረታ ሠነድ ማስገቢያ ቦታ በክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ቢሮ ቁጥር 30 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።

9. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0933800793 ይጠቀሙ፤

የጋምቤላ ሕ/ብ /ክ/መ/ፋይናንስ ቢሮ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-14
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-14 12:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Region: Gambela
  • Publishing entity: Gambela National Regional State Finance Office
  • Bid bond: 30,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 26, 2026)
  • Posted at: 2026-09-28T09:06:26.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders