Textile, Garment and Leather

የቦሌ አዲስ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2019 ዓ.ም የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የግዢ መለያ ቁጥር 001/2019

የቦሌ አዲስ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2019 ዓ.ም ከመንግስት በተመደበልን መደበኛ በጀት እና ውስጥ ገቢ, በጀት 1ኛ ዙር ጥቅል ግዢ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የሎት ቁጥር

የዕቃው ዝርዝር (ዓይነት)

1

ሎት 1

የመምህራን ገዎን ደንብ ልብስ የጥበቃ ጫማ እንዲሁም የሠራተኞች የደንብ ልብስ

2

ሎት 2

አላቂ የቢሮ (የጽህፈት) መሳሪያዎች

3

ሎት 3

አላቂ የህክምና እቃዎች (የመጀመሪያ ህክምና እርዳት መስጫን ጨምሮ)

4

ሎት 4

አላቂ የትምህርት ማበልጸጊያ (የማእከል) የቤተሙከራና የስፖርት እቃዎች እንዲሁም የቧንቧና የኤሌክትሪክ መለዋወጫ እቃዎች

5

ሎት 5

አላቂ የጽዳት እቃዎች

6

ሎት 6

ልዩ ልዩ መሳሪያዎች

7

ሎት 7

የጥገና የኤሌክትሪክ እና የቧንቧ እቃዎች

8

ሎት 8

ቋሚ እቃ እና ለህንጻ አገልግሎት የጥገና እቃዎች

ስለዚህ ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

1. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)ያላቸው ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና በፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር በአቅራቢያዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና ከድህረ ገጽ ላይ የአቅራቢነት ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

2. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸው ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ክሊራንስ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።

3. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ናሙና በዝርዝር በማቅረብ አለባቸው።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid bond) በየሎቱ ብር 5000.00 (አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO የባንክ ዋስትና እንዲሁም በጥሬ ገንዘብ ማቅረብ አለባቸው።

5. ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከት/ቤቱ የ/ክ/ፋ/ግ/ን/ አስተዳደር መውሰድ ይችላሉ።

6. በሎት ቁጥር 7፡ ለተጠቀሱት ስራዎች ተጫራቾች በቦታው ተገኝታችሁ ዝርዝር መረጃ ከት/ቤቱ ፋ/ግ/ን/አስ/ ማግኘት ትችላላችሁ።

7. ተጫራቾች በሌሎች ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ የለባቸውም።

8. ተጫራቾች ያላቸውን መረጃዎችና ሰነዶች አሟልተው በታሸገ ኢንቨሎፕ በት/ቤቱ ፋ/ግ/ን አስተዳደር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ከቀኑ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

9, ጨረታው የሚከፈተው 11ኛው ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ባለው የስራ ቀን 11፡30 በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

10. ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ ለሆኑባቸው ዕቃዎች ከአጠቃላይ ዋጋ ብር 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከት/ቤቱ ጋር የግዢ ውል ስምምነት መፈፀም ይኖርባቸዋል።

11. መ/ቤቱ ለጨረታው ባወጣው ጠቅላላ ዋጋ 20% ከፍ ወይም ዝቅ ብሎ የግዢ ትዕዛዝ ሊሰጥ ይችላል።

12. ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርት ሳያሟሉ በጨረታ ለመሳተፍ መሞከር በህግ ያስቀጣል።

ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ፡-

ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በአካል ት/ቤቱ ድረስ በመቅረብ ያነጋግሩን። አድራሻ፡- ሲኤምሲ አልታድ ሚካኤል ከመስጊድ ወረድ ብሎ ፊጋ መብራቱ ሲደርሱ ወደ ጎሮ በሚወስደው መንገድ ከቦሌ አዲስ የመጀ /ደ/ት/ቤት አጠገብ

ለበለጠ መረጃ፡

011-6-59-60-90 እና 011-6-59-60-61

የቦሌ አዲስ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-09
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00
  • Bid opening: 2026-10-09 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: የቦሌ አዲስ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Bid bond: 5000.00 ብር በየሎቱ
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 27, 2026)
  • Posted at: 2026-09-28T09:42:38.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders