Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በአቃቂ ቃሊቲ ከ/ከተማ የወረዳ 5 ፋይናንስ ፅ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በአቃቂ ቃሊቲ ከ/ከተማ የወረዳ 5 ፋይናንስ ፅ/ቤት የ2019 በጀት ዓመት የሚያስፈልጉ እቃዎች ዝርዝር
- ሎት 1 የፅዳት እቃዎች
- ሎት-2 የፅህፈት መሳሪያ
- ሎት 3 የደንብ ልብስ
- ሎት-4 ቋሚ እቃዎች
- ሎት 5 የትራንስፖርት አገልግሎት
- ሎት-6 ዘር ግብአት
- ሎት-7 አላቂ እቃ
- ሎት-8 መድረክ ማስዋብ
- ሎት 9 የተሽከርካሪ ጎማ
- ሎት- 10 የቢሮ መስተንግዶ
ከዚህ በላይ የተዘረዘሩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በዚሁ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን አሟልቶ በግልፅ ጨረታ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
- ተጫራቾች በንግድ ምዝገባ የተመዘገቡና በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ከሃገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀትና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር ሁለት መቶ (200.00) በመክፈል በአቃ/ቃ/ክ/ከ/ወ5 ፋይናንስ ጽ/ቤት ሁለተኛ (2ኛ) ፎቅ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ሎት-1 የፅዳት እቃዎች 10,000
- ሎት-2የፅህፈት መሳሪያ 10,000
- ሎት-3 የደንብ ልብስ 15000
- ሎት-4 ቋሚ እቃዎች 30,000
- ሎት-5 የትራንስፖርት አገልግሎት 5,000
- ሎት 6 ዘር ግብአት 5,000
- ሎት-7 አላቂ እቃ0,000
- ሎት-8 መድረክ ማስዋብ 2,000
- ሎት-9 የተሽከርካሪ ጎማ 5,000
- ሎት-10 የቢሮ መስተንግዶ 5,000
ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በየሎቱ ብር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተረጋገጠ (CPO) ማስያዝ ኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ውስጥ ቃሊቲ ከአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ወረድ ብሎ ከውሃ ልማት ጎን በሚገኘው ወረዳ 5 ፋይናንስ/ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ (200.00) ሁለት መቶ ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የወሰዳችሁትን የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በማሸግ ኢንቨሎፕ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
4. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
5. ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል፡፡
6. የጨረታው መክፈቻ ቀን በኛው ቀን ሆኖ ነገር ግን ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ወይም በአል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰአት ጨረታው ይከፈታል፡፡
7. የጨረታው አሸናፊ ጽ/ቤቱ ባቀረበው መጠን ወይም ብዛት እቃዎችን ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
8. የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ያሸነፈበት የጠቅላላ ዋጋ 10% ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል በአነስተኛና ጥቃቅን የተደራጀ ከሆነ አምራች የሆነ ብቻ ሲሆን አምራች መሆኑና የሚያመርተው እቃ ተጠቅሶ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
9. ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉት በጨረታው ሰነድ ላይ በተጠቀሰው ስፔስፊኬሽን ሞዴል መሰረት ብቻ ነው፡፡
10.ተጫራቾቸች የሚያቀርቡትን እቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ ከሁለት ቀናት በፊት የማቅረብ ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡
11. ማንኛውም ተጫራቾች በሚያቀርበው እቃ (ናሙና ላይ የተለየ ምልክት ወይም የድርጅቱን ማህተም ማድረግ የተከለከለ ነው::
12. እያንዳንዱ ሰነድ ላይ ማህተም እና የሞሉት የዋጋ ማቅረቢያ ላይ የተጫራቾች ፊርማና የድርጅቱ ማህተም መኖር አለበት፡፡
13. የጨረታው አሸናፊ ውል ከተፈጸመበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበት እቃ በሙሉ በራሱ ትራንስፖርትና ሰራተኛ በማውረድና በማጓጓዝ ባቀረበው ናሙና መሰረት በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ለንብረት ክፍል ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
14. ለሚገቡ የቋሚ እቃዎች ለአንድ ዓመት ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
15.ሰነዱን ሲሞሉ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
16.ስርዝ ድልዝ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡ እንዲሁም ለአንድ እቃ ከአንድ ዋጋ በላይ ማቅረብ አይፈቀድም፡፡
17.ዋጋ ተወደደብኝ እቃው ጠፋብኝ ማለት የማይቻል መሆኑ መታወቅ ያለበት መሆኑና ያስያዙት ሲፒኦ የሚወረስ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ቃሊቲ አሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ወረድ ብሎ ውሃ ልማት አጠገብ የወረዳው ጽ/ቤት ሁለተኛ ፎቅ ፋይናንስ ጽ/ ቤት ይገኛል፡፡
ለበለጠ መረጃ
በስልክ ቁጥር፡- 0913382003 /0923286082/0923481386
በአቃቂ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-09
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-09 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Akaki Kality Sub City Woreda 5 Finance
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 27, 2026)
- Posted at: 2026-09-28T10:39:08.000Z
- Source: Qelal Tenders