Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ አስተዳደር የኮሎኔል አብዲሳ አጋ ጤና ጣቢያ ለ2019 በጀት ዓመት የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በን/ስ/ላ/ክ/ ከተማ አስተዳደር የኮሎኔል አብዲሳ አጋ ጤና ጣቢያ ለ2019 በጀት ዓመት የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን በግዥ መለያ ቁጥር 1/2019 ማለትም
- ሎት 1 አላቂ የቢሮ ዕቃ
- ሎት 2 ቋሚ እቃ
- ሎት 3 የደንብ ልብስ
- ሎት 4 መድኃኒትእና የሕክምና ዕቃ
- ሎት 5 የጽዳት እቃ
- ሎት 6 ህትመት
- ሎት 7 ጥገና አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም
- ለሎት 1 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 11,500
- ለሎት 2 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15,000
- ለሎት 3 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 6,500
- ለሎት 4 ለሎት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10.000
- ሎት 5. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 11,000
- ሎት 6 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 7000
- የጨረታ ለሎት 7 ማስከበሪያ ብር 9,500 ከጨረታው ሰነድ ጋር በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት ፡-
1. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በየሎቱ ብር 150 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) ብቻ በመከፈል ሰነዱን ከጤና ጣቢያው ቢሮ ቁጥር 408 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
3. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን 11፡30 ድረስ አየር ላይ ውሎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌኔል አብዲሳ አጋ ጤና ጣቢያ መሰብሰቢያ አዳራሽ ጨረታው ይከፈታል።
4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) የሥራ ቀናት በጤና ጣቢያው ግዥቢሮ ቁጥር 404 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል
5. ተጫራቾች ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ለሎት 01፣ ለሎት 03 ለሎት ለሎት4 እና 6 ናሙና ማቅረብ አለባቸው ለሎት 2 ፣ ለሎት 5፣ ሎት7፣ በተቋሙ የፍላጎት መግለጫ መሰረት ብቻ ይሆናል።
6. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
7. የዘገየ ጨረታ እና በጨረታ መክፍቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም።
8. አሸናፊ ተጫራቾች የአሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሳችሁ ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መሥሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
9. ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉበሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡-
ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ኮሎኔል አብዲሳ አጋ ጤና ጣቢያ በድሮው ስም ወረዳ 5 ጤና ጣቢያ ልዩ ቦታው ጎፋ ካምፕ አካባቢ ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-462-3253 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ኮሎኔል አብዲሳ አጋ ጤና ጣቢያ
Tender details
- Deadline: 2026-10-08
- Bid closing time: 17:30
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን 11፡30 ድረስ
- Bid opening: 2026-10-09 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: ኮሎኔል አብዲሳ አጋ ጤና ጣቢያ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 150.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published on: Addis Zemen (Sep 27, 2026)
- Posted at: 2026-09-28T10:42:18.000Z
- Source: Qelal Tenders