Equipment and Accessories
በሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት የኮዬ ፈጬ ክ/ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የተለያዩ ቋሚ፣ አላቂ፣ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ እና የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Equipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and Accessories
Oromia
More tags
IT and TelecomOffice Machines and AccessoriesOffice Supplies and ServicesStationeryTextile, Garments and UniformsTextile, Garment and LeatherShoes and Other Leather ProductsCleaning and Janitorial Equipment and ServiceOffice FurnitureFurniture and FurnishingAmharic2merkatoSheger City High Court, Koye Feche Sub-City woreda Court
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት የኮዬ ፈጬ ከ/ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በ2019 የበጀት አመት
- የተለያዩ ቋሚ፣ አላቂ፡
- የፅህፈት መሳሪያዎች፣
- የፅዳት ዕቃዎች፣
- የደንብ ልብስ እና
- የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሞሉ ሕጋዊ ድርጅቶች መወዳደር ትችላላችሁ።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመካፈል ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከ100,000ብር ለሆነ ግዥ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- በገንዘብና ትብብር ልማት ሚኒስቴር ወይም በሌላም በሚመለከታቸው ፈቃድ ሰጪ አካላት በአቅራቢነት የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው ተጫራቾች ብቻ መካፈል ይችላሉ።
- ተጫራቾች ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የስራ ቀናት በማይመለስ 100 ብር መግዛት ይችላሉ።
- ፍ/ቤቱ ካቀረበው መስፈርት /standard/በታች ማቅረብ አይቻልም።
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፁትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችልም።
- ፍ/ቤቱ የሚያጫርታቸውን ዕቃዎች ብዛት እንደ አስፈላጊነታቸው (50%) በመጨመር ወይም በመቀነስ ማዘዝ ይችላል።
- ጨረታው የሚቆየው ለተከታታይ 15 ቀናት ይሆናል። በ15ኛው ቀን 11፡30 ተዘግቶ በነጋታው በ4፡30 ሰዓት ተጫራቶቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
- ማንኛውም ተጨራች በጨረታ ተካፋይ ለመሆን ተመላሽ የሚሆን ባቀረበው ጠቅላላ ዋጋ ላይ 1% የጨረታ ማስከበርያ /CPO/ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል።
- ፍ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ፍ/ቤቱ የሚያጫርታቸውን ዕቃዎች ብዛት ለተከታታይ 6 ወራት ውል ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ይዋዋላል።
- የሚገዙ ዕቃዎች በተሠጠው እስፔስፊኬሽን መሠረት ተሞልተው ካልቀረቡና ማንኛውም ዓይነት ስህተት ቢፈፀም ሃላፊነቱ የአቅራቢው ድርጅት ነው።
አድራሻ፡
ቱሉ ዲምቱ አደባባይ ዩንሳ የሚወስደው መንገድ አሌክስ ተብሎ የሚጠራ አካባቢ የሚገኝ
የፍርድ ቤቱ ፎቅ 5 ቁጥር የፋይናንስ ክፍል ያገኙናል።
ለተጨማሪ መረጀ በስልክ ቁጥር፡ 09-24-11-38-72
በሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት
የኮዬ ፈጬ ክ/ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-14
- Bid closing time: 17:30
- Bid closing (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-15 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ተዘግቶ በነጋታው በ4፡30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Sheger City High Court, Koye Feche Sub-City woreda Court
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 27, 2026)
- Posted at: 2026-09-28T10:43:37.000Z
- Source: Qelal Tenders