Tri Wheeler, Motorcycles and Bicycles Purchase
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለ2019 በጀት ዓመት ለሴክተር መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚሰጡ ሞተር ሳይክሎችን እና ቶታል እስቴሸን በዘርፉ የተሰማሩ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Tri Wheeler, Motorcycles and Bicycles PurchaseConstruction Machinery and EquipmentConstruction and Water Works
Central Ethiopia
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለ2019 በጀት ዓመት ለሴክተር መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚሰጡ ሞተር ሳይክሎችን እና ቶታል እስቴሸን በዘርፉ የተሰማሩ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም፡-
- ሎት 1 ሞተር ሳይክል
- ሎት 2 ቶታል እስቴሽን
- የዘመኑን የታደስ የንግድ ሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል
- የአቅራቢነት ምዝገባ ሠርተፊኬት ማቅረብ የሚችል
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ
- የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 ብር 70,000 (ሰባ ሺህ) እና ለሎት 2 ብር 20,000(ሃያ ሺህ) ለየብቻ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ሰነዱን ከስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ) ብር ብቻ በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ሰነዱን በሚገባ በመሙላት ለየብቻ ፋይናንሻል አንድ ኦሪጅናል እና 2 ኮፒ ለየብቻ እንዲሁም ቴክኒካል ዶክመንቱን አንድ ኦርጂናል እና ሁለት ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሳጥኑ በ10ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ 8፡30 ሰዓት መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። 10ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡-
- ተጫራቾች ያቀረቡት የጨረታ ዋስትና ጥያቄው ዋጋ አንሶ ከተገኘ ከጨረታው ይሰረዛል።
- መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 046 771 0586
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የስልጤ ዞን ፋይናስ መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-10-08
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ10ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-08 14:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ10ኛው ቀን በ8፡30 ሰዓት
- Region: Central Ethiopia
- Publishing entity: Silte Zone Finance and Economic Development Command
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published on: Addis Zemen (Sep 27, 2026)
- Posted at: 2026-09-28T10:47:38.000Z
- Source: Qelal Tenders