Others
ፈደንጓ መልሶ ማልማት የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር በሕንፃው ውስጥ የሚገኙ ክፍት ሱቆችን፣ ለዲስፕሌይ/ማስተዋወቂያ የሚያገለግሉ ቦታዎችን፣ ለስቶር ዕቃ ማከማቻ የሚያገለግሉ ክፍሎችን፣ የጥበቃና የጽዳት አገልግሎትን እንዲሁም በሕንፃው ውስጥ ያሉትን የመኪና ማቆሚያ ቦታዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት/ለአገልግሎት ለመስጠት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ፈደንጓ መልሶ ማልማት የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር በሕንፃው ውስጥ የሚገኙ ክፍት ሱቆችን፣ ለዲስፕሌይ/ማስተዋወቂያ የሚያገለግሉ ቦታዎችን፣ ለስቶር ዕቃ ማከማቻ የሚያገለግሉ ክፍሎችን፣ የጥበቃና የጽዳት አገልግሎትን እንዲሁም በሕንፃው ውስጥ ያሉትን የመኪና ማቆሚያ ቦታዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት/ለአገልግሎት ለመስጠት ይፈልጋል።
ስለሆነም ሕጋዊ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው እንዲሳተፉ እንጋብዛለን።
1.የጨረታው ዝርዝር ሁኔታ
1.1 ክፍት ሱቆች፣ ለተለያዩ የንግድ ዘርፎች፣ እንደ ልብስ፣ ጫማ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቢሮ እና ሌሎች ተመሳሳይ ንግዶች ሊያገለግሉ የሚችሉ ክፍት ሱቆች።
1.2 የዲስፕሌይ ማስተዋወቂያ ቦታዎች፡- በዋና ዋና መተላለፊያዎች፣ ኮሪደሮችና ተስማሚ የሕንፃው ክፍሎች ላይ ለዕቃ ማሳያ፣ ለማስተዋወቂያና ለዲስፕሌይ የሚያገለግሉ ቦታዎች፡
1.3 ስቶር/የዕቃ ማከማቻ ከፍሎች፡- ለተለያዩ ዕቃዎች ማከማቻ የሚያገለግሉ ተስማሚና ደህንነታቸው የተጠበቀ ክፍሎች።
1.4 የጥበቃና የጽዳት አገልግሎት ፡- የአክሲዮን ማህበሩን የገበያ ማዕከል ሕንፃ የጥበቃና የጽዳት አገልግሎት በውል ለመስጠት ፈቃድና ልምድ ያላቸው ድርጅቶች።
1.5 የመኪና ፓርኪንግ አገልግሎት፡- አክሲዮን ማህበሩ ባስገነባው ሕንፃ ውስጥ ከምድር በታች
የሚገኙትን ሦስት ወለሎች የመኪና ማቆሚያ ቦታዎችን በኮንትራት ለመስጠት የሚፈልግ ሲሆን፣ ተወዳዳሪዎች በወር ሊከፍሉት የሚችሉትን የኪራይ የአገልግሎት ዋጋ በጨረታ ሰነዱ መሠረት እንዲያቀርቡ ይጋበዛሉ።
2.የተወዳዳሪዎች መስፈርት
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የቫት (VAT) ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ለስቶር ኪራይ ወይም ለግል አገልግሎት የሚወዳደሩ ከሆነ፣ እንደአስፈላጊነቱ የታደሰ መታወቂያ ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ማስከበሪያ CPO ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በድርጅቱ ስም አሰርተው ማቅረብ/ማስያዝ አለባቸው።
- ድርጅቱ ያዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይኖርባቸዋል።
3.የጨረታ ሰነድ አወሳሰድና ማስገቢያ ጊዜ
- የሰነድ መሸጫ ቦታ፦ በአክሲዮን ማህበሩ ዋና ቢሮ፣ ሜክሲኮ ሰንጋ ተራ፣ አክሲዮን ማህበሩ ሕንፃ፣ 4ኛ ፎቅ፡፡
- የሰነድ መሸጫ ጊዜ፦ ይህ ማስታወቂያ ከታተመበት/ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ 7 (ሰባት) ተከታታይ ቀናት በሥራ ሰዓት።
- ጨረታው የሚዘጋበት ቀንና ሰዓት፦ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ፣ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
1. ለበለጠ መረጃ፡- በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፦ 0991 57 30 72/0911 40 09 89/0968 57 70 28 አድራሻ፦ ሜክሲኮ፣ ሰንጋ ተራ፣ ዘ ሮያል ፕላዛ ሕንፃ አጠገብ።
ማስታወሻ፡- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ፈደንጓ መልሶ ማልማት የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-10-05
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከታተመበት/ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ 7 (ሰባት) ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 6፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-05 14:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከታተመበት/ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ 7 (ሰባት) ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: ፈደንጓ መልሶ ማልማት የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር
- Bid bond: 20,000 (ሀያ ሺህ ብር)
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Sep 27, 2026)
- Posted at: 2026-09-28T11:00:45.000Z
- Source: Qelal Tenders