Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ለቡ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የሚያስፈልጉ እቃዎችን ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ለቡ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የሚያስፈልጉ እቃዎችን በግዢ መለያ ቁጥር 01/2019 ማለትም ሎት 01 ቋሚ እቃ፣ ሎት 02 አላቂ የቢሮ እቃዎች ፣ ሎት 03 ደንብ ልብስ ፣ ሎት 04 ትራንስፖርት ፣ ሎት 05 ህትመት፣ ሎት 06 መጽሐፍ፧ ሎት 07 መስተንግዶ ሎት 08 የፅዳት እቃዎች ሎት 09 የጓሮ አትክልት ዘር ሎት 10 የጉልበት አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ

  • 1. ለሎት 01 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 35,915 (ሰላሳ አምስት ሺህ ዘጠኝ መቶ አስራ አምስት ብር ብቻ)
  • 2. ለሎት 02 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 33,500 (ሰላሳ ሶስት ሺህ አምስት መቶ ብር ብቻ)
  • 3. ለሎት 03 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,039 /ሃያ አምስት ሺህ ሰላሳ ዘጠኝ ብር ብቻ)
  • 4. ለሎት 04 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር ብቻ )
  • 5. ለሎት 05 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 8,745 (ስምንት ሺ ሰባት መቶ አርባ አምስት ብር ብቻ)
  • ለሎት 06 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 350 (ሶስት መቶ ሃምሳ ብር ብቻ)
  • ለሎት 07 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 22,876 (ሃያ ሁለት ሺ ስምንት መቶ ሰባ ስድስት ብር ብቻ)
  • ለሎት 08 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 35,000(ስላሳ አምስት ሺህ ብር ብቻ)
  • ሎት 09 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 1,000 /አንድ ሺህ ብር ብቻ/
  • ለሎት 10. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000 /አምስት ሺህ ብር ብቻ /በባንክ በተረጋገጠ ሰነድ (CPO) ከጨረታው ሰነድ ጋር በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

በስራ ዕድል ጽ/ቤት የተደራጁ ነጋዴዎች ባመረቱበት ምርት ወይም አሴት ተጨማሪ ባደረጉበት ብቻ ልዩ ተጠቃሚን የምናስተናግድ መሆኑን እያሳወቅን ፡፡ ወረዳው ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት፡-

1. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ሰነዱን ከወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት 7ኛ ፎቅ ቀርበው መግዛት ይችላሉ።

3. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ድረስ አየር ላይ ውሎ በ10 ቀን ከቀኑ 11፡30 ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳው መሰብሰቢያ አዳራሽ 7 ፎቅ ጨረታው ይከፈታል።

4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ ማሰታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት በወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት 7ኛ ፎቅ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ለሎት 02 ፤ ለሎት 03፣ ለሎት 05፣ ለሎት 06፤ እና ለሎት 08፤ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ለሎት 01 ማለትም ለቋሚ እቃ በወረዳው የፍላጎት መግለጫ /እስፔክ/ መሰረት ብቻ ይሆናል።

6. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለያንዳንዱ ከቫት ጋር ወይም ቲኦቲ ተካቶ ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል

7. የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም

8. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፈባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

9. ወረዳው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 01 ለቡ ፋይናንስ ጽ/ቤት ሲትራ ህንፃ ወይም ከከቤ ኬክ ቤት 200ሜ ገባ ብሎ።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0118 448 675 / 0118 441 161 ደውለዉ ይጠይቁ።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ለቡ ፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-08
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ድረስ አየር ላይ ውሎ በ10 ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-09 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ድረስ አየር ላይ ውሎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Nifas Silk Lafto Sub City Woreda 01 Lebu Finance Office
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 27, 2026)
  • Posted at: 2026-09-28T13:14:26.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders