Cleaning and Janitorial Equipment and Service

የአዲስ አበባ ሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት የ2019 ዓ.ም የበጀት አመቱን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

  • ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያዎች
  • ሎት 2 የፅዳት ዕቃዎች
  • ሎት 3 የደንብ ልብስ ከነስፌቱ

የአዲስ አበባ ሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ከላይ የተዘረዘሩትን የ2019 ዓ.ም የበጀት አመቱን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

1. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢ የተሰጠ ማስረጃ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

2. ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ ለመሆኑ የምስክር ወረቀት /TIN NO/ ማቅረብ አለባቸው።

3. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ሲያስገቡ አብረው የሚወዳደሩበትን ናሙና /Sample/ ማቅረብ አለባቸው።

4. ተጫራጮች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 2000/ሁለት ሺህ ብር/ በአዲስ አበባ ሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ስም CPO በማሰራት ከኦርጅናሉ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን መወዳደሪያ ሰነድ ቢሮ ቁጥር 7/O-011 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ እየከፈሉ መውሰድ ይችላሉ።

6. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ለውጥ ማሻሻያ ማድረግ እና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም።

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶችን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘውትር በስራ ሰዓት ሰባተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 7/O-06 በመቅረብ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

8. ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል።

9. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ ስማቸው፣ፊርማቸውን እና አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው።

10. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።

አድራሻ፡- ሜክሲኮ ሰንጋተራ ከዘመን ባንክ ጀርባ አዲስ ሲኒማ ማእከል

ስልክ ቁጥር ፡- 09 86 87 87 82 / 09 11 60 15 56

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-08
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት
  • Bid opening: 2026-10-09 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቆይቶ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa Cinema Houses Administration Enterprise
  • Bid bond: 2,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 27, 2026)
  • Posted at: 2026-09-28T13:20:45.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders