Vehicle and Machinery Sale

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አ.ማ. ንብረት በግልጽ ጨረታ አወዳድር በመሸጥ ገንዘቡን ወደ ተበዳሪው የብድር ዕዳ ገቢ ለማድረግ ይፈልጋል

Description

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አ.ማ ከዚህ በታች ስማቻው ለተገለጸው ተበዳሪ የበደረውን ገንዘብ በብድር ውሉ መሠረት ስላልከፈሉ ባንኩ በተሸሻለው አዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለብድር መክፈል ዋስትና እንዲሆን ሥልጣን ባለው አካል የተመዘገበውንና ያሳገደውን ንብረት በግልጽ ጫረታ አወዳድር በመሸጥ ገንዘቡን ወደ ተበዳሪው የብድር ዕዳ ገቢ ለማድረግ ይፈልጋል።

በመሆኑም ማንኛውም ተጫረቾች ሐራጁ በሚካሄድበት ዕለት ተሸከርከሪውን መግዛት የሚፈልጉ በጫረታ ቦታ በመቅረብ በጫረታ ላይ እንዲወዳደሩ ተጋብዟል።

ተ.ቁ

የተበዳሪው ስም

የንብረት አስያዥ ስም

ተሸከርካሪ ዓይነት

ቅርንጫፍ

ለጨረታ የቀረበው የተሸከርካሪ መለያ ቁጥር

የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር

ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ፣ ቀን እና ሰዓት

የሰሌዳ ቁጥር

የሻንስ ቁጥር

የሞተር ቁጥር

የሞዴል ቁጥር

1

አባ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግ.ማህበር

አባ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግ.ማህበር

ጀፓን ቶዮታ (የተሰረበት ዘመን እ.አ.አ 2021)

አዳማ

ኢት-03-A14474

JTMHV01J8 M4326526

IVD0570845

VDJ200- GNTAZV

14,500,000.00

ጫራታው ጥቅምት 3 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት ከ4፡00-6፡00 ሰዓት ኢ.አ ከተማ ቂርቆስ ክ/ከ/ወረዳ 09 ጌት ሀውስ ሕንጻ በኦሮሚያ ብ/ክ/መንግስት ጽ/ቤት ፊት ለፊት የሚገኝ የኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ ፊንፊኔ ቅርንጫፍ የሚገኝበት ሕንፃ 3ኛ ፎቅ የስብሰባ አደራሽ ውስጥ ይካሄዳል::

2

ኮርነር ስቶን ፋርም ኃ.የተ.የግ.ማህበር

መልካም ኢንትግሬትድ ፋርምስ ኃ.የተ.የግ.ማበህር

ልዩ ተንቀሳሽ (መቀዝቀዣ ያለው) የቻይና ሲኖትረክ

ሳርስ

አ.አ- 03-A34257

LZZ5BB FH2RE536680

YC4E160- 33*E3717R10269

FSR33 (2024)

7,000,000.00

ጫረታው ጥቅምት 3 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት ከ8፡00-10፡00 ሰዓት ኢአ ከተማ ቂርቆስ ክ/ከ/ወረዳ 09 ጌት ሀውስ ሕንጻ በኦሮሚያ ብ/ክ/መንግስት ጽ/ቤት ፊት ለፊት የሚገኝ የኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ ፊንፊኔ ቅርንጫፍ የሚገኝበት ሕንፃ 3ኛ ፎቅ የስብሰባ አደራሽ ውስጥ ይካሄዳል::(የጉሙሩክ ቀረጥ እና ታክስ ያልተከፈለ በመሆኑ ገዥ ይከፍለል)

ተጫራቾች ለጫረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች በመገንዘብ ማክበር ይኖርባቸዋል።

1. ተጫራቾች ጫረታው በሚካሄድበት ዕለት የጫረታውን መነሻ ዋጋ 1/4 (25%) የጫረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በባንክ ክፍያ ማዘዣ CPO በኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አ.ማ ስም አሰርተው ይዘው በመቅረብ በጫረታው ዕለት ቀርበው በመመዝገብ በጫረታው ለመሳተፍ ይችላሉ:: ጫረታውን በድርጅት ስም የምጫረት ተጫራች በዘመኑ የታደሰ የንግድ ምዝገበ ወረቀት፣ የንግድ ፈቃድና ከድርጅቱ የተሰጠዉ ውክልና እንዲሁም ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ ማቅረብ አለበት።

2. ጨረታው ከላይ ቦታ፣ ቀንና ሰዓቱ በተገለፀው መሠረት ባለዕዳዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይካሄዳል:: ባለዕዳዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ሳይገኙ ቢቀሩ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።

3. ንብረቱን በሥራ ሰዓት መጎብኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች ተሸከርካሪውን የባንኩ ብድር መገገሚያ እና ፖርትፎሊዮ እና አዳማ ቅርንጫፍ በስልክ ቁጥር 0917-66-39-40 ወይም 0919-58-53-44 እንዲሁም ልዩ ተንቀሳቀሽ ሲኖ ትራክ ለመግዘት የመፈልጉ ተጫራቾች በስልክ ቁጥር 0917-366842 ወይንም 0917- 663940 በመደወል ተሽከርካሪው በሚገኝበት ቦታ በመገኘት በሥራ ሰዓት መጎብኛት ይችላሉ።

4. የጫረታው አሸናፊ የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ የመክፈል ግዴታ አለበት:: የጫረታው አሸናፊ የሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ያስያዘው CPO ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጫረታው ተሰርዞ አዲስ የሐራጅ ማስታወቂያ ወጥቶ የሚካሄድ ይሆናል:: በጫረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረጋል።

5. የጨረታው አሸናፊ በሕጉ መሠረት ለመንግስት የሚከፈለውን ማንኛውንም የቫትና ታክስ ክፍያ፣ የስም ማዛወሪያ እና ሌሎች ወጪዎችን ከፍሎ ስሙ ወደ እራሱ እንዲዛወር ያደርገል:: እንዲሁም በሰንጠረዡ ውስጥ በተረ ቁጥር 2 ላይ የተጠቀሰው ልዩ ተንቀሳቀሽ ሲኖ ትራክ የታርገ ቁጥር አ.አ-03-A34257 የጉሙሩክ ቀረጥ የልተከፈለ በመሆኑ ገዣው የጉሙሩክ ቀረጥ እና ታክስ የሚከፍል መሆኑን እንገልጻለን።

6. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አ.ማ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-13
  • Bid closing time: 16:00
  • Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-10-13 16:00
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Cooperative Bank of Oromia S.C.
  • Buyer address: Dembel City Center
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Reporter (Sep 27, 2026)
  • Posted at: 2026-09-28T13:51:49.000Z
  • Buyer website: https://coopbankoromia.com.et/
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders