Stationery
ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት የተለያዩ እቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 027/19
ድርጅታችን ለሥራ አገልግሎት የሚጠቀምባቸውን ልዩ ልዩ ግብዓቶች ማለትም Yellow Bank Paper 61x86cm 45gm ብዛት 1,500,000 ቅጠል፣ White Wood Free Paper 61x86cm 70gm ብዛት 1,300,000 ቅጠል፣ Wood Free 60gm 42cm ብዛት 100,000 ኪ.ግ፣ White Wood Free Paper 84cm 80gm ብዛት 200,000 ኪ.ግ እና Leather Board Paper 70x100cm 600gm ብዛት 3,000 በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ወቅታዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የገንዘብ ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ምዝገባ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅቱ ዋና መ/ቤት (አራት ኪሎ) አዲሱ ህንፃ 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የዕለት ገንዘብ ተቀባይ የማይመለስ ብር 500.00 በባንክ ከፍለው በመግዛት የፋይናንሺያል እና የቴክኒካል የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውን እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ ነባሩ ህንፃ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው።
ጨረታው 17/02/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ የቴክኒካል መጫረቻ ሰነድ (ከላይ የተገለፁ ለቅድመ ግምገማ የሚያገለግሉ ዶክመንቶች የጨረታ ማስከበሪያ) ብቻ ከሰዓት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ነባሩ ህንፃ 6ኛ ፎቅ በሚገኘው በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬከቶሬት ቢሮ ይከፈታል። የፋይናንሸያስ የመጫረቻ ሠነዶች የሚከፈቱት የቴክኒካል ሰነዳቸው ተቀባይነት ላገኙት ብቻ ነው። ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም።
ስልክ ቁጥር 011-155-5230
ድረ ገፅ www.ethbspe.org
Berhanena selam printing enterprise አዲስ አበባ
ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-10-27
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-10-27 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Berhanena Selam Printing Enterprise
- Buyer address: Addis Ababa, Ethiopia
- Bid bond: 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Sep 28, 2026)
- Posted at: 2026-09-29T07:28:30.000Z
- Source: Qelal Tenders