Printing and Publishing

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 028/19

ድርጅታችን ለስራ አገልግሎት የሚጠቀምባቸውን ልዩ ልዩ ግብአቶች ማለትም Fountain Solution ብዛት 3,000 ሊትር፣ Round Bright Stiching Wire No 20 ብዛት 2,000 ጥቅል፣ Gum Thermal CTP Plate ብዛት 1,000 ኪ.ግ እና Black Web Offset lnk 25kg ብዛት 5,000 ኪ.ግ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ወቅታዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የገንዘብ ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ምዝገባ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስከር ወረቀት፤ የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ከሊራንስ ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅቱ ዋና መ/ቤት (አራት ኪሎ) አዲሱ ህንፃ 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የዕለት ገንዘብ ተቀባይ የማይመለስ ብር 500.00 ከፍለው በመግዛት የፋይናንሺያል እና የቴክኒካል የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውን እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ ነባሩ ህንፃ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000 በባንክ ከፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው።

ጨረታው በ17/2/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ የቴክኒካል መጫረቻ ሰነድ (ከላይ የተገለፁ ለቅድመ ግምገማ የሚያገለግሉ ዶክመንቶች፣ የጨረታ ማስከበሪያ) ብቻ ከሰዓት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ነባሩ ህንፃ 6ኛ ፎቅ በሚገኘው በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል።  የፋይናንሽያል የመጫረቻ ሠነዶች የሚከፈቱት የቴክኒካል ሰነዳቸው ተቀባይነት ላገኙት ብቻ ነው። ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም።

ስልክ ቁጥር 011-155-5230
ድረ ገፅ www.ethbspe.org 
Berhanena selam printing enterprise አዲስ አበባ
ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-27
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-10-27 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Berhanena Selam Printing Enterprise
  • Buyer address: Addis Ababa, Ethiopia
  • Bid bond: 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ) ብር
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 28, 2026)
  • Posted at: 2026-09-29T07:29:23.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders