Stationery

በምዕራብ አርሲ ዞን በገደብ ሀሳሳ ወረዳ መስተዳድር የገደብ ሀላላ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በምዕራብ አርሲ ዞን በገደብ ሀሳሳ ወረዳ መስተዳድር የገደብ ሀላላ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  1. የጽህፈት መሳሪያዎች እና የጽዳት ዕቃዎች
  2. የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች
  3. የቴክኒክ እና ሙያ ማሰልጠኛ የመማሪያ መሳሪዎች
  4. የሰራተኞች የደንብ ልብስ
  5. የመኪና እና ሞተር ጎማዎች

በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው።

1. ተጫራቾች ከሚጫረቱበት ዕቃ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለውና ዕቃዎቹን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል ህጋዊ ንግድ ፈቃድ እንዲሁም የ2019 ዓ.ም የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱና TIN No እንዲሁም የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

2. ተጫራቾች በጨረታ ተካፋይ ለመሆን የምትፈልጉት በምን ዓይነት ዕቃ ላይ እንደሆነ በሰነዶቻችሁ ላይ በትክክል ለይተው መጻፍ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የዕቃ ስም (Brand Name) እና የተመረተበትን ሀገር መግለጽ ይኖርባቸዋል።

4. ማንኛውም ተጫራች የሚወዳደርበትን የዕቃ አይነት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ማቅረብ ይኖርበታል። በነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ቢኖር የነጠላ ዋጋ ይወስዳል።

5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 19/01/2019-09/02/2019 ዓ.ም ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 250.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ) ብር በመክፈል የጨረታ ሰንዱን ከገደብ ሀሳሳ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት መግዛት የምትችሉ መሆኑን ይገልጻል።

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲሞሉ ከነቫት መሆኑና አለመሆኑን በግልጽ በመጥቀስና የድርጅታችሁን ማህተምና ሙሉ አድራሻችሁን በመግለጽ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ዘወትር በስራ ሰዓት በቢሮ ቁጥር 3 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ተመላሽ የሚሆን ለእያንዳንዱ ሰነድ 5000 ብር በባንክ በተመሰከረለት CPO ወይም በጥሬ ብር በገደብ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

8. የሚቀርቡት ዕቃዎች ጥራት ያላቸው እና በእስፔስፊኬሽን መሰረት ተሟልተው መቅረብ ይኖርባቸዋል።

9. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት ገደብ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።

10. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ16ኛው ቀን ማለትም 10/02/2019 ዓ.ም የስራ ቀን ጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት 4፡00 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤታችን ቢሮ ቁጥር 3 ይከፈታል። ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ጠዋት 4፡00 ሰአት የሚከፈት ይሆናል።

11. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታወን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

12. አሸናፊ ተጫራቾች የአሸነፉትን እቃዎች አጠቃላይ ዋጋውን 10% ቢድ ቦንድ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

13. ተጫራቾች VAT ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

14. የደንብ ልብስ ሲቀርብ የምታቀርቡትን አይነት ናሙና መቅረብ ይኖርበታል።

15. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 12 25 35 76/ 09 13 81 93 89 መደወል ይችላሉ።

በምዕራብ አርሲ ዞን በገደብ ሀሳሳ ወረዳ መስተዳድር የገደብ ሀሳሳ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-20
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid opening: 2026-10-20 10:00
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: West Arsi Zone Gedeb Hasasa Woreda Finance Office
  • Bid bond: ለእያንዳንዱ ሰነድ 5000 ብር
  • Bid document price: ለእያንዳንዱ ሰነድ 250 /ሁለት መቶ ሃምሳ ብር /
  • Published on: Addis Zemen (Sep 29, 2026)
  • Posted at: 2026-09-29T08:31:05.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders