House and Building Foreclosure

የቤቶች ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍርድ ባለመብት ግርማዬ በላይ እና በፍርድ ባለእዳ እነ ወ/ሮ አስናቀች መንገሻ መካከል ስላለው አፈፃፀም የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ319842 17/11/2017ዓ.ም እና በኮ/ መ/ቁ.329695 በቀን 27/06/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትእዛዝ

1ኛ በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 07 የቤት ቁጥር 066 እና 068 የሆነው የውርስ ሀብት የቤት ቁጥር 066 የተመዘገበው በወ/ሮ የሺወርቅ ወ/ገብርኤል ስም የተመዘገበ ይዞታው ገና መብት ያልተፈጠረለት ቢሆንም በ1988ዓ.ም የአየር ካርታ /ጂ.አይ.ኤስ/የይዞታ ስፋት 84ካሜ የቤቱ ቤቱ/ቦታው/ በ4ቱም አቅጣጫ ያሉ አዋሳኞች በሰሜን የቤት ቁጥር 64፣ በደቡብ የቤት ቁጥር 68 ፣በምሥራቅ የቤት ቁጥር 62 መንገድ፣ በምእራብ የቤት ቁጥር 69 ለሶስተኛ ወገን ስም ንብረት ዝውውር ለማድረግ መብት ያልተፈጠረለት ይዞታ ነው። ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 3,564,552 (ሶስት ሚሊዮን አምስት መቶ ስልሳ አራት ሺህ አምስት መቶ ሃምሳ ሁለት ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል። 

2ኛ የቤት ቁጥር 068 የተመዘገበው በወ/ሮ ምትኬ ሙሉጌታ ወ/አብ ስም የተመዘገበ ይዞታው ገና መብት ያልተፈጠረለት ቢሆንም በ1988ዓ.ም የአየር ካርታ ጂ.አይ.ኤስ የይዞታ ስፋት 101 ካ.ሜ የቤቱ ቤቱ /ቦታው/ በ4ቱም አቅጣጫ ያሉ አዋሳኞች በሰሜን የቀበሌ ቤት፣ በደቡብ የቀበሌ ቤት፣ በምሥራቅ የቀበሌ ቤት መንገድ፣ በምእራብ ስዩም ማሞ ለሶስተኛ ወገን ስም ንብረት ዝውውር ለማድረግ መብት ያልተፈጠረለት ይዞታ ነው። ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 4,272,378 (አራት ሚሊየን ሁለት መቶ ሰባ ሁለት ሺህ ሶስት መቶ ሰባ ስምንት ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.PO ማስያዝ ይኖርበታል። 1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት CPO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 11 273 0852
በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-04
  • Bid closing time: 11:00
  • Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-11-04 11:00
  • Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Court Judicial Procedure Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Addis Zemen (Sep 29, 2026)
  • Posted at: 2026-09-29T08:49:20.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders