Textile, Garments and Uniforms

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የምዕ/ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

የብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መ/ቁጥር .. ምዕ/ግ/ ጨ / A-01/19

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የም/ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በዳንሻ እና ነቀምት ከተማ ውስጥ በሚገኙ ግምጃ ቤቶች ውስጥ የሚራገፉ የተለያዩ አይነት ፡-

  1. ዳንሻ ከተማ የሚራገፉ አልባሳት እና ጫማዎች፣
  2. ዳንሻ ከተማ የሚራገፉ አላቂ የቢሮ የፅሕፈት መሳሪያዎች፤
  3. ዳንሻ ከተማ የሚራገፉ የትምህርትና ስልጠና መርጃ ዕቃዎች፤
  4. ዳንሻ ከተማ የሚራገፉ የህሙማን ቀለቦች፤
  5. ዳንሻ ከተማ የሚራገፉ አላቂ የፅዳት ዕቃዎች፣
  6. ዳንሻ ከተማ የሚራገፉ የቅስቀሳ እና ፕሮፓጋንዳ ዕቃዎች
  7. ዳንሻ ከተማ የሚራገፉ የማሽነሪና የጀነሬተር ጥገና መለዋወጫ ዕቃዎች፤
  8. ነቀምት ከተማ የሚራገፉ አላቂ የቢሮ የፅሕፈት መሳሪያዎች ሲሆኑ፤

ከላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በ1ኛው ዙር ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፤ በመሆኑም በዚህ ጨረታ ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ፡-

1) አግባብ ያለው በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤

2) የቫት ሰርተፍኬት፤

3) የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ፤

4) በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ መሆኑን ማስረጃ ፤

5) በጨረታ እንዲሳተፉ ከገቢ ሰብሳቢ መስሪያ ቤት ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፤

6) በንግድ ስያሜው መሰረት የተዘጋጀና የተረጋገጠ 15 ቀን ያልሞላው የባንክ ስቴትመንት ማቅረብ የሚችል፤

7) የጨረታ ማስከበሪያ (2%)፡- ከባንክ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ አለባቸው፤

የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በካሽ ዳንሻ በሚገኘው የምዕ/ዕዝ ግዥ ቢሮ በመምጣት ወይም በኢ/ያ ን/ባንክ አካውንት ቁጥር 1000478536945

በwestern command HQ ስም በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከመስከረም 21/01/2019 ዓ/ም ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ

የጨረታ ማስረከቢያ (CPO) መጠን

  1. አልባሳት እና ጫማዎች -11,990.18
  2. አላቂ የቢሮ የፅሕፈት መሳሪያዎች-50,874.87
  3. የትምህርትና ስልጠና መርጃ ዕቃዎች-23,691.00
  4. የህሙማን ቀለበት-143,711.19
  5. አላቂ የፅዳት ዕቃዎች-135,140.92
  6. የቅስቀሳ እና ፕሮፓጋንዳ ዕቃዎች-1,999.38
  7. የማሽነሪና የጀነሬተር ጥገና መለዋወጫዎች-19,803.00
  8. ነቀምት የሚራገፉ የፅሕፈት መሳሪያዎች፣-12,765.00

ጨረታው ሀሙስ ጥቅምት 05/02/2019 ዓ/ም ከረፋዱ 3፡00 ሠዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ጨረታው ሀሙስ ጥቅምት 05/02/2019 ዓ/ም ከረፋዱ 3፡30 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዳንሻ ከተማ በሚገኘው የምዕራብ ዕዝ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።

  • ተጫራቾች የአንዱን ዕቃ ዋጋ ከመሙላታቸው በፊት በጨረታ ሰነዱ ላይ የቀረበውን ስፔስፊኬሽን በአግባቡ ማንበብ አለባቸው።
  • ተጫራቾች የአንዱን ዕቃ ዋጋ በራሳቸው ዋጋ ማቅረቢያ ላይ ከሞሉ በኋላ የሚያቀርቡትን ዕቃዎች ብራንድ ስሪት ወይም የዕቃውን ጥራት ደረጃ በግልፅ ተሞልቶ ማህተም ተደርጎበት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻው መቅረብ አለበት።
  • ተጫራቾች ለጨረታ ሲመጡ በጨረታ ሰነዱ ላይ በሞሉት የዕቃዎች ስሪት መሰረት የዕቃዎችን ሳምፕል (ናሙና) ማቅረብ አለባቸው።
  • መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ ህጋዊ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ፡- ስልክ 057 660 3275 0913631100 መደወል ይቻላል
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የምዕ/ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ
ዳንሻ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-15
  • Bid closing time: 09:00
  • Bid opening: 2026-10-15 09:30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Ministry of Defense
  • Buyer address: መከላከያ ት/ስልጠና ዋ/መ/ግዥ ቡድን ጃል ሜዳ ታቦት ማደሪያ ፊት ለፊት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Oct 01, 2026)
  • Posted at: 2026-10-01T07:32:20.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders