Textile, Garment and Leather

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በአዳማ ሪጅን ስር ለሚገኙ የሥራ ክፍሎች እና በሰላሳ(30) አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ለሚገኙ የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች የሚውል የተለያዩ አይነት የሰራተኞች ደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች ለማሰፋት ይፈልጋል

Description

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር ኢ/ኤ/አ/አ/ሪ/ግ/ጨ/002/2019

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በአዳማ ሪጅን ስር ለሚገኙ የሥራ ክፍሎች እና በሰላሳ(30) አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ለሚገኙ የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች የሚውል የተለያዩ አይነት የሰራተኞች ደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች ለማስፋት ይፈልጋል።

የዕቃው አይነት

የመዝጊያ ቀን እና ሰዓት

የመክፈቻ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ ዋስትና መስከበሪያ

የተለያዩ 5(አምስት) አይነት የሰራተኞች ደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት ግዥ

ጥቅምት 6 ቀን 2019 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት

ጥቅምት 6 ቀን 2019 ዓ.ም 8፡30 ሰዓት

ብር 75,000.00 (ሰባ አምስት ሺ)

1 ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨ.እታ፣ የግብር ከፋይ መ/ቁጥር እና ከገቢዎች ባለስልጣን ጽ/ቤት ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ የሚል ማስረጃ ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል።

2. ተጫራቾች የመንግስት ድርጅቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ እንዲችሉ በግዥ ኤጀንሲ ድህረ-ገፅ ላይ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው።

3. በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማያያዝ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ዝርዝር ሁኔታው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ይገኛል።

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000150084613 EEU-Customer Contribution በሚለው ገቢ በማድረግ እና የከፈሉበትን የባንክ ስሊፕ ይዞ በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።

5. አድራሻ፡- አዳማ እየሱስ ቤ/ክርስቲያን አጠገብ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በአዳማ ሪጅን ሰፕላይ ቼይን ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 04 ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን ከላይ በሠንጠረዡ ውስጥ በተገለፀው መሠረት ሆኖ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ሲፒኦ /CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Bond) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል «ኦሪጅናል እና ኮፒ በማለት በተለያየ ፖስታ በማሸግ እና ሁለቱን በአንድ ትልቅ ፖስታ በማድረግ የጨረታ ቁጥር፡- ኢ/ኤ/አ/አ/ሪ/ግ/ጨ– 002/2019 የሚል ምልክት በማድረግ እስከ ጥቅምት 6 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ድረስ ከላይ በተራ ቁጥር 5 ላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን ጥቅምት 6 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።

7. ጨረታው ከላይ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

8. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 022-111-2091(022-211-4625) መደወል ይችላሉ።

10. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የአዳማ ዲስትሪክት ኤሌክትሪክ አገልግሎት

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና መ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-16
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-10-16 14:30
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Ethiopian Electric Utility
  • Bid bond: 75,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 01, 2026)
  • Posted at: 2026-10-01T07:47:27.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders