Equipment and Accessories

ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገቢዎች ባለሥልጣን የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገቢዎች ባለሥልጣን በ2019 በጀት ዓመት

  • ሎት 1 ኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ግዥ፣
  • ሎት 2 እስቴሽነሪ እና ሌሎች አላቂ እቃዎች ግዥ ፣
  • ሎት 3 ፈርኒቸር ዕቃ ግዥ፣
  • ሎት 4 የጽዳት ዕቃዎች፣
  • ሎት 5 ሞተርሳይክል ግዥ፣እና
  • ሎት 6 የመኪና ጥገና አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ ድርጅት በጨረታው እንዲሳተፍ እየጋበዝን በጨረታው ላይ ለመካፈል አቅራቢው ቀጥሎ የቀረቡት መመዘኛዎች ወይም መስፈርቶች ማሟላት አለበት፡፡

1. በዘርፉ የታደሰ ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ፣ የአቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀትያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው የሚገልፅ መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡

2. ጨረታዉ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት ቀናት ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡

3. የጨረታውን ዝርዝር ሁኔታ የሚያመላክት የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውሰጥ የንግድ ፈቃዳቸውን በመያዝ ቀርበው ከቢሮ ቁጥር 06 በ200 መቶ ብር በመግዛት መውሰድ ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች ለውድድር ሲቀርቡ ለጨረታ ማስከበሪያ ሎት 1 = 30,000, ሎት 2 = 10,000 ሎት 3 = 25,000, ሎት 4 = 5,000, ሎት 5 = 10,000 እና ሎት 6 = 25,000 በባንክ በተመሰከረ CPO በፖስታ አሽገው ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ተቀባይነት የለውም፡፡

5. ጨረታዉ 16ኛው ቀን ከጧቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 በክልሉ ገቢዎች ባለሥልጣን ግዥ/ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ቀኑ በዓል ወይም የእረፍት ቀናት ከሆነ በሚቀጥለው በሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ይከፈታል፡፡

6. ተጫራቾች የፋይናንሻል የቴክኒክ መገምገሚያ መስፈርት በመሙላትና በተለያየ ሁለት ኦርጅናል ፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የፋይናንስ የቴክኒክ መሆኑን በመግለጽ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

7. ተጫራቾች የሰጡት ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክሰ ማካተት አለማካተቱን በፋይናንሻል ጨረታ ዋጋ ማቅረቢያው ላይ በግልጽ ማሳየት ይጠበቅባቸዋል፡፡

8. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን አልወዳደርም ማለት አይችልም፡፡

9. የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ማሸነፉ በፅሁፍ ከተገለጸለት በኋላ በ7 የስራ ቀናት ውስጥ ለውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተመሰከረ CPO በመያዝ ከመ/ ቤቱ ጋር ውል መፈራረም አለበት፡፡ ውሉን ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ቀርቦ ባይገባ ባይፈጸም/ የጨረታ አሸናፊነቱ ይሰረዛል፡፡

10. የጨረታው አሸናፊ የሆነ ድርጅትን ወክሎ ውሉን የሚፈርም የድርጅቱ ባለቤት ሳይሆን ቀርቶ ተወካይ ከሆነ ህጋዊ ውክልና ኦርጅናልና የማይመለስ ኮፒ ይዞ መቅረብ አለበት፡፡

11. ለጨረታው የውል ማስከበሪያ የተያያዘው ገንዘብ አሸናፊው ተጫራች ግዴታውን በሙሉ መሰረት ካልፈጸሙ በሙሉ ላይ በሚገልጸው ህግ መሰረት መ/ቤቱ ተፈፃሚ የማድረግ መብት አለው፡፡

12.ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዕቃ ወይም አገልግሎት የአያንዳንዱ ዋጋ ሞልተው የሚያቀርቡት በፋይናንሻል በጨረታ ሰነዱ ሳይ በሚገኘው የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም መሙያ ውስጥ ብቻ መሆን አለበት፡፡

13. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀነዉ፡፡

አድራሻ : ሀዋሳ የዱሮ ደህዴን ጀርባ እንገኛለን፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 046 212 5156 ይደውሉ፡፡
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገቢዎች ባለሥልጣን


Tender details

  • Deadline: 2026-10-19
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን ከጧቱ 4፡00
  • Bid opening: 2026-10-19 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን ከጧቱ 4፡30
  • Region: Sidama
  • Publishing entity: Sidama National Region State Revenue Authority
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Oct 01, 2026)
  • Posted at: 2026-10-01T07:54:44.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders