Stationery

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 01/2019

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎችን፣ የፅዳት እቃዎችን፣ የደንብ አልባሳትን ቋሚ ዕቃዎች እና የኅትመት የአገልግሎት፣ የትራንስፖርት አገልግሎት እና የኪራይ አገልግሎቶች ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከሎት 1-7 ለተጠቀሱት ዕቃዎችና የአገልግሎት ግዥ ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ በዝርዝር የተቀመጡትን ነጥቦች በሚገባ ተረድተው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በሎት በእያንዳንዱ ሎት በመሙላት መወዳደር ይችላሉ።

ተ.ቁ

ሎት

የግዥው ዓይነት

ናና በተመለከተ

የሲፒኦ መጠን በብር

የመዝጊያ ቀንና ሰዓት

የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

ሎት- 1

የጽሕፈት መሣሪያዎች ግዥ

መቅረብ አለበት

20,000.00

ጥቅምት 5 ቀን 2019 ዓ.ም 4፡30 ሰዓት

ጥቅምት 5 ቀን 2019 ዓ.ም 5፡00 ሰዓት

2

ሎት-2

የፅዳት ዕቃዎች ግዥ

መቅረብ አለበት

20,000.00

3

ሎት-3

የደንብ ልብስ አልባሳት ግዥ

መቅረብ አለበት

20,000.00

4

ሎት-4

የቋሚ ዕቃዎች ግዥ

ስፔስፊኬሽን

10,000.00

5

ሎት-5

የኅትመት አገልግሎት ግዥ

-

5,000.00

6

ሎት-6

የትራንስፖርት አገልግሎት

-

5,000.00

7

ሎት-7

የኪራይ አገልግሎቶች/ ዲኮርና ሌሎችም

-

5,000.00

1. በጨረታው መሳተፍ የሚችሉት

  • በዘርፉ የተሰማሩ እና የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣
  • የዘመኑን ግብር የከፈሉ ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፣
  • የግብር ከፋይ መለያ /TIN No./ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  • በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና
  • የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ተመዝጋቢ የምሥክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

2. የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቀርበው በመግዛት መውሰድ ይችላሉ።

3. ከአነስተኛና ጥቃቅን ማኅበራት በአምራችነት ተደራጅታችሁ መወዳደር የምትፈልጉ ካላችሁ ካደራጃችሁ አካል በጽ/ቤት ኃላፊ የዋስትና ደብዳቤ ማስረጃ ማምጣት አለባችሁ፡፡ የራሳቸው ምርት ካልሆነና ገዝተው ለሚያቀርቡት ዕቃ የጨረታ ሰነድ መግዣና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከላይ በሰንጠረዥ በተገለጸው መሠረት በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማስያዝ አለባቸው።

5. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ የተጠቀሰውን አገልግሎት የአንዱን መለኪያ ዋጋ 15% የተ.እ.ታ. ጨምሮ በዋጋ ማቅረቢያው ላይ በመሙላት ማቅረብ አለባቸው።

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን የተለያዩ ኢንቨሎፖች ኦሪጂናልና ፎቶ ኮፒ ሰነዶች ለያይተው በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። በተጨማሪም አንድ ኮፒ በማሸግ ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ በወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7. የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ሐሙስ ጠዋት ከ2፡30 እስከ 6፡30 ከሰዓት በኋላ ከ 7፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ዓርብ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 5፡30 ከሰዓት በኋላ ከ 7፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ነው።

8. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ በወጣበት ማስታወቂያ መሠረት ከላይ በሰንጠረዥ በተገለጸው ቀን እና ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙት ይከፈታል፤ ዘግይቶ የመጣ ተጫራች ተቀባይነት የለውም ።

9. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ:- ከመገናኛ ጎሮ አደባባይ ፍሊት ስቶን ከጎሮ ሳይት ሳይደርሱ ከድልድዩ በስተቀኝ ያገኙታል።

ስልክ ቁጥር 0118 664 855

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-15
  • Bid closing time: 10:30
  • Bid opening: 2026-10-15 11:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Lemi Kura Sub City Woreda 09 Administration Finance Office
  • Buyer address: ከመገናኛ ሰፈራ አደባባይ ፍሊት ስቶን ጎሮ ሳይት ሳይደርሱ ከድልድዩ በስተቀኝ ያገኙታል
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 01, 2026)
  • Posted at: 2026-10-01T08:11:36.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders