Stationery
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የነሽ ሜዳ ቧንቧና ፕላስቲክ ማምረቻ ድርጅት የተለያዩ እቃዎችን በብሄራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታዎቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
StationeryOffice Supplies and ServicesTextile, Garments and Uniforms
Amhara
More tags
Textile, Garment and LeatherShoes and Other Leather ProductsCleaning and Janitorial Equipment and ServiceEquipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsMechanicalConsumable GoodsRaw materialsPlastic ProductsPlastic Raw Materials and ProductsPlastic Raw MaterialsAmharic2merkatoGosh Meda Plastic and Pipe Manufacturing Enterprise
Description
ብሄራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ጨ/001/2019
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የነሽ ሜዳ ቧንቧና ፕላስቲክ ማምረቻ ድርጅት በ 2019 በጀት ዓመት ለድርጅቱ ስራ ማስፈጸሚያ የሚውሉና ቀጥለው የተዘረዘሩትን እቃዎችን ማለትም ፡-
|
ሎት |
የጨረታው ዓይነት |
|
1 |
የቢሮ አላቂ እቃዎችን (የጽህፈት መሳሪያዎችን) |
|
2 |
የደንብ ልብስና ተዛማጅ ቁሳቁሶችን |
|
3 |
የጽዳት እቃዎችን (ሌሎች አላቂ እቃዎችን) |
|
4 |
ለምርት ማምረት ስራ የሚያገለግሉ አላቂ እቃዎችን |
በብሄራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታዎቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ድርጅቱ ይጋብዛል።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊና አግባብነት ያለው ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN ያላቸው፣
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታከስ VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፣
- ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የማመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸው።
- የሚገዙ የእቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን | ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶችን ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 500.00/ አምስት መቶ ብር/በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ጎሽሜዳ ቧንቧና ፕላስቲክ ማምረቻ ድርጅት ደሴ ገራዶ ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በመቅረብ መግባት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ / ለሚወዳደሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ /ቫቱን/ ጨምሮ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው ደረቅ ቼክ ማስያዝ አይቻልም፡፡
- አንድ ተጫራች በአንድ ሎት ዉስጥ ከተዘረዘሩት የዕቃ አይነቶች መካከል ከፋፍሎ መጫረት አይቻልም። ሆኖም በሎቱ ውስጥ ከተዘረዘሩት ዕቃዎች ዉስጥ አንድ ዕቃ ዋጋ ሳይሰጥበት ቢቀር ተጫራቹ ድርጅት ከጨረታ ውጪ የሚሆን ይሆናል፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን /ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 21 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ጎሽ ሜዳ ቧንቧና ፕላስቲክ ማምረቻ ድርጅት ቢሮ ቁጥር 6 በመገኘት ለዚህ ጉዳይ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጎሽ ሜዳ ቧንቧና ፕላስቲክ ማምረቻ ድርጅት ቢሮ ቁጥር 6 ጨረታው በጋዜጣ በወጣበት በ21ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ላይ በይፋ ይከፈታል።
- ድርጅቱ ጨረታውን የሚያወዳድረው በሎት ነው።
- ድርጅቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ተወዳድሮ አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ያሸነፋቸውን እቃዎች ድርጅቱ ወደሚገኝበት ደሴ ገራዶ አግሮስቶን ቅጥር ግቢ ድረስ የሚያቀርብ ይሆናል።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09 62 99 99 33/ 09 14 60 11 39/ 09 14 05 26 33 / 09 91 84 19 10/ 09 30 87 87 84 በመደወል ወይንም በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይቻላል።
አድራሻ : ደሴ ገራዶ ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ደሴ የግንባታ ግብዓት ማምረቻ
ማዕከል ቅጥር ግቢ
የጎሽ ሜዳ ቧንቧና ፕላስቲክ ማምረቻ ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-10-22
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 21 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-22 10:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 21 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Gosh Meda Plastic and Pipe Manufacturing Enterprise
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published on: Addis Zemen (Oct 02, 2026)
- Posted at: 2026-10-02T07:59:49.000Z
- Source: Qelal Tenders