Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋርዱላ ዞን የጊዶሌ ከተማ አስተዳደር ፋ/ፕ/ል/ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ ግዥዎችን መፈጸም ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋርዱላ ዞን የጊዶሌ ከተማ አስተዳደር ፋ/ፕ/ል/ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ከሚፈፅማቸው ግዥዎች መካከል፡-

  • ሎት 1. የጽሕፈት መሣሪያዎችንና ሌሎች ዓላቂ የቢሮ ዕቃዎችን እና
  • ሎት 2. የደንብ ልብስ /የሥራ ልብስ ግዥዎችን

ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን ከሚያሟሉ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ፡-

  • በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው።
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ።
  • የአቅራቢዎች ምዝገባ የምስክር ወረቀት /ኦን ላይን/ ያላቸው።
  • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN No/ ያላቸው።
  • የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ጨረታ 25,000 ብር ከታወቀ ባንክ ሲ.ፒ.ኦ/ በጥሬ ገንዘብ ማቅረብ የሚችሉ።
  • ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከጊዶሌ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቅ/ጽ/ቤት በመቅረብ ለአንዱ ጨረታ የማይመለስ 200 ብር በመክፈል መግዛት አለባቸው።
  • የገዙትንም ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በማዘጋጀት በሁለት የተለያዩ በታሸገ ፖስታ በማሸግ ኦርጅናሉ ላይ ኦርጅናል ኮፒው ላይ ኮፒ ብሎ በመፃፍ ፊርማና ማህተም በማሳረፍ ይህ ማስታወቂያ በዚህ ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ እስከ 15ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ብቻ ማስገባት አለባቸው 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡ ጨረታው በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ላይ በጊዶሌ ከተማ አስተዳደር ፋ/ፕ/ል/ጽ/ቤት ይከፈታል።
  • የተጫራቾች በሰዓቱ ያለመገኘት የጨረታውን አከፋፈት አያስተጓጉልም።
  • የጨረታው አሸናፊዎች ተለይተው ከተገለጸ ከ7 ቀናት በኋላ በ5 ቀናት ውስጥ አሸናፊዎች የውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ ውል መግባት አለባቸው፡፡ ተሸናፊዎች ደግሞ ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ መውሰድ ይችላሉ።
  • አሸናፊዎች በገቡት ውል መሠረት ዕቃዎቹን እስከ ጊዶሌ ከተማ አስተዳደር ፋ/ፕ/ል/ጽ/ቤት ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
  • በጨረታ ሰነድ ላይ የተሞሉ ዋጋዎችእስከ 40 ቀናት ድረስ ፀንተው መቆየት ይኖርባቸዋል።
  • መ/ቤቱ ከጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ፡- ስልክ 0467 740 564 / 536 ይደውሉ

የጊዶሌ ከተማ አስተዳደር ፋ/ፕ/ል/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-16
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በዚህ ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በዛው ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-16 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በዚህ ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በዛው ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: Gidole City Administration FEDB
  • Bid bond: 25,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Bid document price: 200.00 ብር ለአንዱ ጨረታ
  • Published on: Addis Zemen (Oct 02, 2026)
  • Posted at: 2026-10-02T08:05:28.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders