Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የግዥና ንብ/አስ/ጠቅ/አገ/ዳይሬክቶሬት በ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

/የጨረታ ቁጥር 001/2019

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የግዥና ንብ/አስ/ጠቅ/አገ/ዳይሬክቶሬት በ2019 በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ተ.ቁ

ሎቶች

የዕቃው ዓይነት

የሚያስዙት የጨረታ ማስከበሪያ/CPO

1

ሎት 1

አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች ግዥ

5,000

2

ሎት 2

አላቂ የጽዳት ዕቃዎች ግዥ

3,000

3

ሎት 3

የደንብ ልብስ እና የፕሮቶኮል ልብስ ግዥ

4,000

4

ሎት 4

ቋሚ ዕቃዎች/ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ

10,000

5

ሎት 5

የመኪና ፣ የጎማና ጌጣጌጥ ግዥ

6,000

6

ሎት 6

የጥናት አገልግሎት

100,000

7

ሎት 7

የማስታወቂያ አገልግሎት እና የመድረክ ዝግጅት አገልግሎት

4,000

8

ሎት 8

የመኪና ኪራይ አገልግሎት

10,000

9

ሎት 9

የመኪና ጥገና አገልግሎት

5,000

10

ሎት 10

የህትመት አገልግሎት

3,000

11

ሎት 11

የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና አገልግሎት

3,000

12

ሎት 12

የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት

500

መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፡-

1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው መሆኑን፣

2. የዘመኑን ግብር የከፈለ መሆን አለበት፣

3. የተጨማሪ እሴት ታከስ/የቫት/ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማቅረብ የሚችል፣

4. የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ያለው፣

5. የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር/ Tin No ያለው፣

6. ተጫራቾች በባንክ የተረጋገጠ በጽ/ቤታችን ስም CPO ማስያዝ አለባቸው ነገር ግን CPO ያላስያዘ ቢኖር ከጨረታ ውጪ ይሆናል፣

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት የሚችሉት ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ይሆናል።

8. ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ለመወዳደር ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ዕቃዎች ናሙና መቅረብ አለበት።

9. ማንኛውም ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1 እስከ 5 የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ፒያሳ/ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው ማዘጋጃ ቤት የከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ፋይናንስ ዳይሮክቶሬት ቢሮ የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፣

10. አሸናፊው ድርጅት ጥራቱን ያልጠበቀ ዕቃ ወይም አገልግሎት ካቀረበ በራሱ ወጪ የመለወጥ ግዴታ አለበት፣

11. መ/ቤቱ ካቀረበው ሰነድ ውጪ በሌላ ሰነድ በአማራጭነት ማቅረብ አይቻልም፣ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ቴክኒካል ኦርጅናል እና ፋይናንሽያል ኦርጅናል ዋጋ ሞልታችሁ በተናጠል /ለየብቻ/ እንዲሁም ቴክኒካል ኮፒ እና ፋይናንሽያል ኮፒ በፖስታ አድርጋችሁ የድርጅታችሁን ማህተምና ፊርማ በማድረግ በግዥና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 342 ለጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባችሁ፣

12. ጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች ለምትጫረቱባቸው ዕቃዎች የጨረታ ሰንዱን በነፃ ለመውሰድ

ሀ. ካደራጃችሁ መ/ቤት ደብዳቤ ማምጣት አለባችሁ፣

ለ. ሰነዱን በነፃ ለመውሰድ በመመሪያ መሰረት ለምታቀርቡት ዕቃ አምራች መሆን አለባችሁ፣

13. ተጫራቾች ጽ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት በትክክል መሙላት አለባቸው፣

14. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ አሸናፊው ድርጅት ባሸነፈበት ዕቃ ወይም አገልግሎት ላይ ውል ሲገባ የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል፣እንዲሁም አሸናፊ የሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት ጨረታ ተከፍቶ ውጤት ከተለጠፈ ከ8 የሥራ ቀናት በኋላ በመ/ቤታችን ቀርቦ ውል መግባት አለበት፣

15. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ጋዜጣው ከወጣበት ከ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል። ነገር ግን 11ኛ ቀን የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለው የሥራ ቀናት ውስጥ የሚከፈት ይሆናል።

ማሳሰቢያ፡-

1. ተጫራቾች የቀረበው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆኑንና ያላካተተ መሆኑን መግለጽ አለባችሁ ይህ ካልሆነ ግን መ/ቤቱ የቀረበውን ዋጋ ቫትን እንዳካተተ አድርጎ ይወስደዋል።

2. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ማዘጋጃ ቤት /ከንቲባ ግቢ ውስጥ/ ክፍለ ከተማ አራዳ ወረዳ 1 ፒያሳ ምንይልክ አደባባይ /ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን/ ፊት ለፊት

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0118 680 464 ይደውሉ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-14
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ጋዜጣው ከወጣበት ከ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-14 14:30
  • Bid opening (note): ጋዜጣው ከወጣበት ከ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa Administration Head Office
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 02, 2026)
  • Posted at: 2026-10-02T08:19:21.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders