Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ/ 01/2019

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የደንብ ልብስ ፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የህትመት ውጤቶች፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣ የመረጃ ቴክኖሎጅ ዕቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የመፀዳጃ ቤት ጥገና ዕቃዎች፣ የመኪና ጌጣጌጥ ዕቃዎች እና የመረጃ ቴከኖሎጅ ዕቃዎች የጥገና እና የሰርቪስ አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፀውን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትሳተፉ ይጋብዛል።

1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና Tin ሰርተፍኬት ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ።

2. ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና መረጃ ያላቸው።

3. ጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ ከገቢ ሰብሳቢ መ/ቤት ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4. ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምሥክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በየሎቱ የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት አንድ የደንብ ልብስ ብር 3,200.00 (ሶስት ሺህ ሁለት መቶ ብር)፣ ለሎት ሁለት አላቂ የጽህፈት ዕቃዎች 13,000.00 (አስራ ሶስት ሺህ ብር)፣ ለሎት ሦስት የህትመት ውጤቶች ብር 9,000 (ዘጠኝ ሺህ ብር)፣ ለሎት አራት ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች 7,500.00 (ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብር)፤ ለሎት አምስት የመረጃ ቴክኖሎጅ ዕቃዎች 18,700.00 (አስራ ስምንት ሺህ ሰባት መቶ) ብር ብቻ ሎት ስድስት የፅዳት ዕቃዎች ብር 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር)፤ ሎት ሰባት የመፀዳጃ ቤት የጥገና ዕቃዎች 4,800.00 (አራት ሺህ ስምንት መቶ ብር)፣ሎት ስምንት የመኪና ጌጣጌጥ ዕቃዎች 5,900.00 (አምስት ሺህ ዘጠኝ መቶ) ብር፣ ሎት ዘጠኝ የመረጃ ቴክኖሎጅ ዕቃዎች የጥገና እና ሰርቪስ አገልግሎት ግዥ 3,000.00 (ሶስት ሺህ ብር) ሲፒዮ (CPO) ወይም የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው።

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ በቅሎ ቤት (ግሎባል ሆቴል ፊት ለፊት) ዳቢ ቤኛ ታወር 1ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የቅ/ጽ/ቤታችን ግዥና ፋይናንስ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 102 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናሉንና ኮፒውን ለብቻ በማድረግ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ቅዳሜን ጨምሮ ጋዜጣው ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅ/ጽ/ቤቱ አንደኛ ፎቅ ግዥና ፋይናንስ ቢሮ ውስጥ ይከፈታል።

8. የጨረታው መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ላይ ካልዋለ ቀጥሎ ባለው መደበኛ የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ሲሆን ይከፈታል።

9. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር፡- 011 470 5241 / 011 470 5817

አድራሻ፡- በቅሎ ቤት ግሎባል ሆቴል ፊት ለፊት ዳቤ ቤኛ ህንፃ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 102

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-14
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-14 12:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa Revenue and Customs Authority Higher Tax Payers Branch Office
  • Buyer address: በቅሎ ቤት ግሎባል ሆቴል ፊት ለፊት ዳቢ ቤኛ ህንፃ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 102
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 02, 2026)
  • Posted at: 2026-10-02T08:22:28.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders