Equipment and Accessories
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በከተማ ውስጥ የመብራት መስመር ዝርጋታ ሥራዎች እና የተበላሹ የመንገድ መብራቶች ጥገና ለማከናወን LED Street Light 120W power እና Power Cable 2x2.5mm 2 ግዥን ለመፈጸም አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Equipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsInstallation, Maintenance and Other Engineering Services
Sidama
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በሀዋሳ ከተማ አስ/ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ መሠረት በከተማ ውስጥ የመብራት መስመር ዝርጋታ ሥራዎች እና የተበላሹ የመንገድ መብራቶች ጥገና ለማከናወን LED Street Light 120W power እና Power Cable 2x2.5mm˄2 ግዥን ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ያስፈለገ በመሆኑ በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች መካከል አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት፦
- በዘርፉና ተመሳሳይ ሥራ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው ፣
- በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣
- ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣
- በጨረታው እንድሳተፍ የታክስ ከሊራንስ ማቅረብ አለበት፣
- የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው ፣
- የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተ ዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ (ከተማ አስተዳደር ህንፃ) አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 (ሃምሳ አራት) በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /ለአሥር/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርባችሁ ሰነድ በብር 500(አምስት መቶ ብር) በመግዛት ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንከ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲፒ ኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ (ፋይናንሻል) በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10(አሥር) ተከታታይ ቀናት በፋይ/ኢኮ/ልማ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ ኬዝ ቲም ) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከቀኑ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከቀኑ 4.00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል። ይህ ቀን በበዓላት፣ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል። የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
- አንድ ተጫራች በስሙ ከአንድ ሰነድ በላይ መግዛት አይችልም፣
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 046-212-1334
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና /ኢኮ/ል/መምሪያ
ሀዋሳ
Tender details
- Deadline: 2026-10-12
- Bid closing time: 09:30
- Bid closing (note): ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 3፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-12 10:00
- Bid opening (note): ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት
- Region: Sidama
- Publishing entity: Hawassa City Administration Finance & Economic Development Bureau
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 02, 2026)
- Posted at: 2026-10-02T08:33:45.000Z
- Source: Qelal Tenders