Textile, Garments and Uniforms

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአራዳ ክ/ከተማ የመሀል ግንፍሌ የመጀ/ደ/ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት አመት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 01/2019 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአራዳ ክ/ከተማ የመሀል ግንፍሌ የመጀ/ደ/ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት አመት ነጭ የጋውን የደንብ ልብስ ፖሊስተር 6000፣ የደንብ ልብስ ካኪ ፖሊስተር 6000፣ ቦቢሊን ጨርቅ፣ ቆዳ ጫማ የወንድና የሴት፣ የስፖርት ቱታ እና ሸራ ጫማ የሴት፣ ቱታ የአትክልተኛ፣ ሸሚዝ እጀ ሙሉ፣ የፕላስቲክ ቦቲ ጫማ፣ የሱፍ ካፖርት፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ የትምህርት እቃዎች፣ ሌሎች አላቂ እቃዎችና አቅርቦቶች፣ ከለር ፕሪንተር፣ ቴሌቪዥን፣ ሞንታርቦ፣ እስካነር፣ ፍሪጅ፣ ሬዲዮ፣ የተለያዩ ጠረጴዛዎች፣ የተለያዩ ወንበሮች፣ ፋይል ካብኔት ባለብረት፣ ኤል ሼፕ ሶፋ፣ ጥቁር ሰሌዳ እና ሌሎች ተዛማጅ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና የሠራተኞች የደንብ ልብስ ስፌት ማሰፋት ይፈልጋል።

ተጫራቾች የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት ይገባቸዋል።

1. በተሰማሩበት የሥራ መስክ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር /TIN NO/ ያላቸው፣ ሕጋዊ ደረሰኝ ያላቸው፣ በአቅራቢ ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል።

2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው። 

3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተመሰከረለት CPO (ሲፒኦ) ብር 5000.00/አምስት ሺህ ብር/ በመስሪያ ቤቱ ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማየት ናሙና የሚቀርብባቸውን እቃዎች ናሙና ማቅረብ ናሙና የማይቀርብባቸውን እቃዎች በከለር ፎቶ የተደገፈ ማስረጃ ከናሙናው ጋር ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5. ጨረታውን የሚያሸንፈው ድርጅት እቃዎቹን እስከ ት/ቤቱ ማድረስ አለበት።

6. ጨረታው አየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ11 (አስራ አንድ) ተከታታይ የሥራ ቀናት ይሆንና በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል። የጨረታውን ሰነድ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ ቫትን ጨምሮ ተሟልቶ ለየብቻው በፖስታ ታሽጎ ሲፒኦ በኦርጅናል ውስጥ በማድረግ ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። የተገዛው የጨረታ ሰነድ ሙሉ በሙሉ በተጫራቾች ዋጋው ተሞልቶ በየገፁ ተፈርሞበት መግባት አለበት።

7. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት ራሳቸው አምርተው ለገበያ በሚያቀርቡት ዕቃ ወይም እሴት ጨምረው ለሚያመርቱት ምርት ካልሆነ በስተቀር የተዘጋጁ እቃዎችን ገዝተው ለሚወዳደሩበት እንደማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ መግዛትና የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

8.ተጫራቾች ስርዝ ድልዝ፣ የማይነበብ ሰነድ፣ የዘገየ ሰነድ፣ጨረታላይያልተነበበ የዋጋ ማቅረቢያ፣ከገዙት ጨረታ ሰነድ ውጭ ተሞልቶ የሚመጣ ሰነድ እና ቀነ ገደብ የሚያስቀምጥ ተቀባይነት አይኖረውም።

9. አሸናፊ ተጫራች 10% የውል ማስከበሪያ CPO (ሲፒኦ) በመስሪያ ቤቱ ስም ማስያዝ አለባቸው።

10. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘውን ሰነድ የማይመለስ 200 ብር /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

11. መሥሪያ ቤቱ ለግዢው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- አራት ኪሎ አለ የስነጥበብና ዲዛይን ት/ቤት ወይም አዲስ የእናቶችና ህፃናት ሆስፒታል አጠገብ

ስልክ ቁጥር፡- 011 123 2840 / 011 154 4531 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
የመሀል ግንፍሌ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-15
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-15 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Mehal Genfele Elementary School
  • Buyer address: አራት ኪሎ አለ የስነጥበብና ዲዛይን ት/ቤት ወይም አዲስ የእናቶችና ህፃናት ሆስፒታል አጠገብ
  • Bid bond: 5000 (አምስት ሺህ ብር)
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Oct 04, 2026)
  • Posted at: 2026-10-05T08:16:38.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders