Textile, Garment and Leather

በኮልፌ ቀራንዮ ከፍለ ከተማ ወረዳ 02 ሕዳሴ የመ/ደ/ት/ቤት በ2019 ዓ.ም የሥራ ዘመን የተለያዩ የቢሮ መግልገያ ቁሳቁስ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 002/19

በኮልፌ ቀራንዮ ከፍለ ከተማ ወረዳ 02 ሕዳሴ የመ/ደ/ት/ቤት በ2019 ዓ.ም የሥራ ዘመን የተለያዩ የቢሮ መግልገያ ቁሳቁስ ማለትም፡-

  • ሎት 1 የደንብ ልብስ
  • ሎት 2. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
  • ሎት 3 ሕትመት
  • ሎት 4. አላቂ የሕክምና ዕቃዎች
  • ሎት 5. አላቂ የት/ዕቃዎች
  • ሎት 6. የጽዳት ዕቃዎች
  • ሎት 7 ልዩ ልዩ መሣሪያዎችና መጽሐፍት
  • ሎት 8. ለፕላንት ለማሽነሪ መግዣ
  • ሎት 9 ቋሚ ዕቃዎች የመሳሰሉትን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

1. ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት / ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሰነድ ማስረጃዎችን ዋናውንና ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።

2. ተጫራቾች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ የሚችሉና ቋሚ ዕቃዎች ገዢው ት/ቤት በአካል መጥቶ ለማየት ከፈለገ ለመተባበር ፍቃደኛ ሊሆኑ የሚችሉ መሆን አለበት።

3. ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ካራ ቆሬ ከሚገኘው የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 በሚገኘው የሕዳሴ የመ/ደ/ት/ቤት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ2፡30–11፡30 ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ ታሽጎ በት/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የሥራ ቀን 2፡30 እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት በት/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 5 ሰነድ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

5. ት/ቤቱ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

6. አሸናፊ ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከቫት ጋር መሆን አለበት።

7. ጥቃቅንና አነስተኛ የሚያመጡት ደብዳቤ በጽ/ቤት ኃላፊ የተፈረመ መሆን አለበት።

8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት 1 ብር 10000 ብር ለሎት 2 ብር 4000 ለሎት 3 ብር 1000 ለሎት4 ብር 1000 ለሎት 5 ብር 4000 ለሎት 6 ብር 8000 ለሎት 7 ብር 4000 ለሎት 8 ብር 12000 ሎት 9 ብር 7000 የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ cpo በመስሪያ ቤታችን ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

9. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን እቃ በሙሉ ለትምህርት ቤቱ ንብረት ክፍል ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

10. የቋሚ ዕቃዎችን መሥሪያ ቤቱ ድረስ ሳምፕል ማምጣት የማይችሉትን በፎቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

አድራሻ፡- በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ሕዳሴ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ልዩ ቦታው ካራ ቆሬ ኮንዶሚኒየም ወይም ቢቂላ መናፈሻ ጀርባ

ስልክ ቁጥር፡- 09 12 12 03 94/ 011 369 4712

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ሕዳሴ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-15
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-15 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ሕዳሴ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Oct 03, 2026)
  • Posted at: 2026-10-05T08:16:46.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders