Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን ማረሚያ ተቋም ለ2019 በጀት ዓመት ለተቋሙ የሚያገለግሉ የተለያዩ ዕቃዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን ማረሚያ ተቋም ለ2019 በጀት ዓመት በመንግሥት ከሚበጀትልን መደበኛ በጀት ላይ ለተቋሙ የሚያገለግሉ በተለያዩ ሰባት ዓይነት ሎቶች የተገለጹትን ዝርዝር ለአንድ ዓመት የሚቆይ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት

  1. ሎት አንድ (1) አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎችና ዕቃዎች
  2. ሎት ሁለት (2) የጽዳት ዕቃዎች
  3. ሎቶ ሶስት (3) ደንብ ልብስ
  4. ሎት ኣራት (4) የመኪና እስፔር ፓርት
  5. ሎት አምት (5) መኪና ጥገና እጅ ዋጋ
  6. ሎት ስድስት (6) ፈርኒቸር
  7. ሎት ሰባት (7) ኤሌክትሮኒከስ አቃ

በዚህ መሠረት በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተቀመጡትን የመጫረቻ መስፈርቶችን ማሟላት አለባቸው

  1. ለሎት አንድ (1)፡- አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎችና ዕቃዎች: 2 ሎት (6) ፈርኒቸር 3ኛ ሎት (7) ኤሌክትሮኒክስ እቃ ፡ሎት(4) የመኪና እስፔር ፓርት 10,000.00 C.PO ማቅረብ አለበት።
  2. ለሎት (2)፡- የጽዳት ዕቃዎች ሎት(3) ደንብ ልብስ ሎት (5) መኪና ጥገና እጅ ዋጋ 5,000 CPO ማቅረብ የሚጠበቅባችሁ ሲሆን ሠነድን ከጨረታ ጋር በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

መስፈርቶች፦

1. በዘርፉ የተመዘገበ ሕጋዊና የታደሰ ንግድ ሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፤

2. ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN NUMBER) ማቅረብ የሚችል፤

3. የአቅራቢነት ምዝገባ ማቅረብ የሚችል

4. ተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም TOT ተመዝጋቢ የሆነ

5 ከክፍያዉ 3% ተቀናሽ በመክፈል ፈቃደኛ የሆነ፣ ነገር ግን ሎት፣ (5) መኪና ጥገና የእጅ ዋጋ አገልግሎት ሰለሆነ አቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ አይጠበቅበትም፤

6. ማንኛውም ተወዳዳሪ ጨረታውን ተወዳድሮ ሲያሽንፍ የግዥውን ጠቅላላ ዋጋ ቢያንስ 10% የውጪ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ክፍያ ማዘዥ / C.P.O / የማቅረብ ግዴታ አለበት።

7. ተጫራቾች የተዘጋጀዉን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በሚዛን ማረሚያ ተቋም በመቅረብ ከፋይናንስ ከፍል ቢሮ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመግዛት የምትጫረቱበትን ዋጋ በመሙላት ቴክኒካልና ፋይናንሻሉን በአንድ በታሸገ ፖስታ በኢንቨሎፕ በማደረግ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት የጠበቅቦታል።

8. ከሎት አምስት ውጭ የሚወዳደሩ ተጫራቾች ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ለሚጫረቱበት ጨረታ ናሙና ይዘው (አያይዘው) ማቅረብ አለባቸው።

9. ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን እስከ 15/02/2019 ዓ/ም ጀምሮ ለ30 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ በቀን 16/02/2019 በሰዓት 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ሚዛን ማረሚያ ተቋም ፋይናንስ ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል። ነገር ግን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና ዕሁድ ከሆነ በመጀመሪያው የሥራ ቀን ወይም ሰኞ የሚከፈት ይሆናል።

10. ጨረታውን ያሸነፈ ድርጅት ማሸነፉ በተገለፀለት በ5 ቀናት ውስጥ ቀርቦ ተቋሙ በሚያዘጋጀው ውል መግባት ያሸነፈውን ጨረታ አስከ ተቋሙ ድረስ አምጥቶ የማስረከብ ግዴታ አለበት።

ማሳሰቢያ

  • ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ጨረታው ክፍት ሆኖ የሚቆየው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15/2/2019 ዓ/ም ጨረታው የሚከፈተው በቀን 16/2/2019 ዓ/ም
  • ማንኛውም ተጫራቾች በጨረታው ላይ በሚሳተፋበት ወቀት ከላይ በቀረበው መስፈርት መሰረት የጨረታ ማስያዢያ CPO/ ማቅረብ አለባቹ።

አድራሻ፡- ሚዛን ማረሚያ ተቋም

ሚዛን ማረሚያ ተቋም


Tender details

  • Deadline: 2026-10-26
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-10-26 14:30
  • Region: South West Ethiopia Region
  • Publishing entity: Mizan Correctional Facility
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Oct 03, 2026)
  • Posted at: 2026-10-05T08:32:23.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders