Textile, Garments and Uniforms

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ የልደታ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የደንብ ልብስ፣ አላቂ የፅዳት ዕቃዎች፣ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የፎቶ ኮፒ እና የፕሪንተር ቀለሞች እና ህትመት የተለያዩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም.

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ የልደታ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት አመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ሎት

የግዥው አይነት ዝርዝር

ምርመራ

1

የደንብ ልብስ

 

2

አላቂ የፅዳት ዕቃዎች

 

3

የጽሕፈት መሣሪያዎች

 

4

የፎቶ ኮፒ እና የፕሪንተር ቀለሞች

 

5

ህትመት

 

 ማሳሰቢያ፡-

  • ስለሆነም ተጫራቾች በዘርፉ የተመዘገቡበትን፣ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃዎችና በመንግስት ግዢ ኤጀንሲ ድህረ-ገፅ ዌብሳይት ላይ በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን ከኢ/ያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባችኋል።
  • ከብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር) በላይ ለማቅረብ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የቫት /VAT/ ተመዝጋቢ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባችሁ።
  • የጨረታ ማስከበሪያ 2% በሲፒኦ /CPO/ ወይም የባንክ ጋራንቲ፣ በጥሬ ገንዘብ የተከፈለበት ደረሰኝ ማቅረብ ይኖርባችኋል።
  • ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እሰከ ሚዘጋበት ቀን ድረስ ለጨረታ ሰነዱ መግዣ ለእያንዳንዱ ሎት /የግዥ አይነት የተቀመጠውን የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር ብቻ የጽ/ቤቱ ክፍያና ሂሳብ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመክፈል ልደታ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የግዢ/ፋ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 06 መውሰድ ይቻላል።
  • ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነዶች ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያየ ፖስታዎች በማሸግ ኦርጅናል እና ኮፒ የሚል ምልክት/ፅሁፍ/ በማድረግ በአንድ ትልቅ ካኪ ፖስታ ታሽገው መቅረብ አለባቸው።
  • የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ፣ የባንክ ጋራንቲ ወይም ጥሬ ገንዘብ የተከፈለበት ደረሰኝ ኮፒ፣ እንዲሁም ለጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅት ካቋቋማቸው አካል የተሰጠ የዋስትና ደብዳቤ ኦርጅናል በታሸገው ፖስታ ውስጥ መካተት አለበት። በኦርጅናልና በቅጅው መካከል ያለመጣጣም ቢከሰት ኦርጅናል የበላይነት ይኖረዋል።
  • በመጫረቻ ሰነዱ የቀረበው ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ዕለት ጀምሮ ለ60 ቀናት የፀና ይሆናል።  ግምገማው ከ60 ቀናት በላይ የሚወስድ ከሆነ ጽ/ቤቱ እንደ አስፈላጊነቱ ግምገማው እስከ ሚጠናቀቅ ድረስ ተጫራቾች ያቀረቡትን የመጫረቻ ዋጋ እንዲያራዝሙ የመጠየቅ መብት ያለው ሆኖ ለማራዘም ፈቃደኛ ያልሆነ ድርጅት ከጨረታው ይሰረዛል።
  • የመጫረቻ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባችኋል። ከተገለጸው ቀንና ሰዓት በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
  • ጨረታዎቹ በተጠቀሰው የመክፈቻ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልፅ የሚከፈት ይሆናል።
  • ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመርኩዞ መጫረት አይችልም።
  • ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10/አስር የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ ከቆየ በኋላ በ11ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  • ጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻው ቀን በበዓል ወይም እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  • በአቅራቢነት ተጫራቾች ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ናሙና እስከ ጨረታ መክፈቻ ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ በተጠየቀባቸው ናሙናቸውን ግዥ ክፍል ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
  • የተጫራቾች ተሟልቶ አለመገኘት የጨረታ አከፋፈት ሥነ-ሥርዓትን አያስተጓጉልም።

ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው። ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቅሬታ መስሚያ ቀናት ቅሬታ ካሎት በጽ/ቤቱ ማቅረብ ይቻላል። እንዲሁም ከ7 የቅሬታው መስሚያ ቀናት በኋላ ባለ 7 የስራ ቀናት ውል መውሰድ የሚችል።

ማስታወሻ፡

  1. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ሰነዱ አንድ አካል ተደርጐ ይቆጠራል።
  2. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ የሰፈሩት ዝርዝር መረጃዎች፣ በተጫራቾች መመሪያ እና ሰንጠረዥ የተዘረዘሩትን ግዴታዎች በትኩረት ማንበብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ላይ ቫትን ካላካተቱ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ ቫትን እንዳካተት ተቆጥሮ ይወሰዳል።

አድራሻ፡-

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ የልደታ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቡልጋሪያ መብቱ ፊት ለፊት ያሬድ አረጋዊ ሕንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 06 እንገኛለን።

ለተጨማሪ ማብራሪያ ስ.ቁ፡- 251 11 130 2919

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ

ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-16
  • Bid closing time: 10:30
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10/አስር የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ ከቆየ በኋላ በ11ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-16 11:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10/አስር የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ ከቆየ በኋላ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 5፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 04, 2026)
  • Posted at: 2026-10-05T09:48:05.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders